ሰናይት የተፀነሰችው መቀሌ ሲሆን፤ ለውልደት የበቃችው ጨርጨር - ራያ ሴት አያቷ ዘንድ ነው።
የሕይወት ጥላ ሆኗት ለዕቅፍ በበቃች በአንድ ወሯ ግጭት ተቀሰቀሰ።
ከእናቷ ጋር ከራያ ወደ መቀሌ ተመለሰች።
ከፍ ብላም አፈር መፍጨት፣ ፊደል መቁጠር ጀመረች።
ሲልም ጆሮዎቿ በአገርኛ ሙዚቃ ተቃኙ። ትከሻዎቿ በባሕላዊ እስክስታ መርገድ ያዙ።
Senayt Mebrahtu (R). Credit: S.Mebrahtu
ዳግም ሌላ ግጭት ተፈጠረ። አፍላ የልጅነት ሕይወቷ ለካርቱም ስደት ተዳረገ።
Senayt Mebrahtu. Credit: S.Mebrhatu.
የቀለም ትምህርቷን ከሙዚቃና ድራማ ጋር አዋድዳ ቀጠለች።
ሕይወት በአገረ አውስትራሊያ
የሰናይት የአውስትራሊያ ሕይወት ጅማሮ ግርታን የተላበሰ ነበር።
ከቋንቋ፣ ባሕልና የአኗኗር ዘይቤው ይልቅ የአገሯን ሰዎች ፈልጋ ማግኘት፤ ሌላው ቀርቶ በቆዳ ቀለም የሚቀራረቧትን እንኳ እንደ ልብ ማየት አለመቻል አዋኪ ስሜትን ፈጠረባት።
የትምህርት ቤት ሕይወቷ ግና በአንዲት ጥያቄ የጥበበ ዕጣ ፈንታዋን ለመቅረፅ በቃ።
ጠያቂዋ መምህርቷ ነበሩ።
ጥያቄያቸውም " ስታድጊ ምን መሆን ትፈልጊያለሽ?" የሚል ነበር።
የሰናይት ምላሽ "ተዋናይት" ሆነ።
ቁም ነገረኛዋ መምህርት የቲአትር ኩባንያ ማፈላለግ ጀመሩ።
ቀናቸው።
ሰናይት ከቲአትር ኩባንያው ጋር ተቀላቀለች።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ምርጫዋ ውስጥ ቲአትርን አካተተች።
የእናቷ ድጋፍ ታከለበት። የመንፈስ ብርታትን አገኘች።
የዩኒቨርሲቲ ሕይወቷም በፈጠራ ትምህርት መታነፅ ቀጠለ።
20 ተዋናዮችን ለላቀ የጥበብ መድረክ የሚያወዳድር ዕድል ገጠማት።
ከ800 አመልካቾች ውስጥ ማጣሪያውን ካለፉት 40 ታሳቢዎች ውስጥ አንዷ ሆነች።
ሆኖም ከ20ዎቹ ውስጥ ሳትካተት ቀረች።
ቀጣዩን ዓመት በትወና የቲአትር ጥናት ትምህርት ቀስማ በቀዳሚ ዲፕሎማ ተመረቀች።
የሰናይት የትወና ሕይወት በረከት የመጣው በአውስትራሊያዊቷ ተዋናይትና ፀሐፌ ተውኔት ሳሊ ማኬንዚ "Scattered Lives" አጭር ተውኔት አማካይነት ነው።
ተውኔቱ የቀረበው ሰናይት በታደመችበት አንድ የምረቃ ቲአትር ዝግጅት ወቅት ነበር።
ጭብጡም የስደተኞችን ሕይወት የሚያንፀባርቅ ነው።
የራሷን የሕይወት ገፅታ በማኬንዚ የብዕር ቀለም ፍስሰት መድረክ ላይ ያየችው ሰናይት ሳሊ ዘንድ ቀርባ ምስጋናዋን አቀረበች።
የሙያ ጉዞ ምኞቷንም ገለጠች።
ሳሊ በሁለት ተዋናዮች በገጠሪቱ ኩዊንስላንድ ላሉ ተማሪዎች የሚተወን "A Safer Place" አጭር ተውኔት እነሆኝ አለቻት።
Senayt Mebrhatu (R). Credit: S.McKenzie
ተጨማሪ ያድምጡ
ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ
ተጨማሪ ያድምጡ
ሰናይትና ኤልቪስ