በነጮች ዓለም የጥቁር ገፀ ባሕሪይን ተላብሶ የመተወን አጋጣሚ ውስን ነው።
ለምን? ቢሉ አንድም የተውኔት ሕይወቱ ምንጭ ገፀ ባሕሪያት የሚቀዱት ከአገሬው ነው፤ ሲልም በነጭ የብዕር ቀለም የጥቁር ዓለምን ነቅሶ የገሃዱን ዓለም ስጋ ማላበስና ነፍስ መዝራት አዋኪ ነውና።
ደግነቱ ግና የሰናይት የጥበብ እስትንፋስ የተመላው በጥበብ ፍቅር እንጂ በዝና ፍለጋ ባለመሆኑ በተግዳሮት ፊት ስኬትን አሳቢ አድርጓታል።
የማኅበረሰቧን መሠረት ባለመልቀቋና ተነጥላም ተንሳፋፊ ባለመሆኗ የአቢሲኒያ ዳንስ ቡድን መሥራች፣ ድምፃዊትና ተወዛዋዥ ሆና ባሕላዊ ዝንቅነትን ለአገረ አውስትራሊያ እነሆኝ አለች።
በተለያዩ ፌስቲቫሎች ላይ ባሕላዊ ሙዚቃና ውዝዋዜዎችን ለመድረክ አብቅታለች።
ሰናይት በአቢሲኒያ የዳንስ ቡድን አልተወሰነችም።
ዘልቃ አንድ ሙዚቃዊ የቲአትር ቡድን ከሌሎች አፍሪካውያን የጥበብ ሰዎች ጋር ተቧድና መሠረተች።የቲአትር ኩባንያና የመድብለ ባሕል ድርጅቶችም "አለን" ብለው ተቀላቀሉ።
Source: Abyssinian Dance Group
በጋራ "i am here" የሚል የአዲስ ሠፋሪዎችን ሕይወት የሚያንፀባርቅ ሙዚቃዊ ድራማ ለመድረክ አበቁ።የአገሬውን ሰው ጨምሮ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ አባላትም ታዳሚዎች ሆኑ።
Actress Senayt Mebrahtu (C). Source: S.Mebrhatu
ስኬት ስኬትን ወለደ።
ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከአገር ቤት እስከ አውስትራሊያ
ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከአገር ቤት እስከ አውስትራሊያ
ከመድረክ ትወና ወደ ቴሌቪዥን ድራማ
የሰናይት የሥነ ጥበብ ኮከብ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ ብርሃኑን ፈነጠቀ።
እ.አ.አ. ከ2010 አንስታ "Terra Nova" ተከታታይ የቴሌቪዥን ሳይንሳዊ ድራማ ላይ ለረጅም ጊዜ ተሳታፊ ሆነች።በተጓዳኝም ሌሎች በርካታ ትወናዎችን እየከወነች ቀጠለች።
Actress Senayt Mebrhatu. Source: Carolina Häggström
ትልቁ የ2022 ሥራዋ ግና የ "Elvis" ሙዚቃዊ ድራማ ትወናዋ ነው።