አቢይ ሳህሌ አበበ፤ ከክርራ እስከ ሳክስፎን

Abiy Sahle Abebe 1.jpg

Saxophonist Abiy Sahle Abebe. Credit: AS.Abebe

አቢይ ሳህሌ አበበ - ነዋሪነቱ ሜልበርን ከተማ ሲሆን፤ በሙያው የሳክስፎን ተጫዋች ነው። የቀድሞው ዝነኛ ክቡር ዘበኛ (አንደኛ ክፍለ ጦር) ኦርኬስትራ ሳክስፎን ተጫዋቹ ሳህሌ አበበ ልጅ ነው። "የሰላም ዜማ" በሚል መጠሪያ አዲስ የሙዚቃ አልበም አውጥቶ ሰሞኑን ለማስመረቅ በመሰናዶ ላይ ይገኛል።


አንኳሮች
  • ውልደትና ዕድገት
  • የአባትና ልጅ የሙዚቃ ፍቅርና የጉዞ ሂደት
  • ከክራር ወደ ሳክስፎን
የአቢይ የትውልድ ቀዬ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አዲስ አበባ ሲሆን፤ የሙዚቀኛ እጆቹንም በክራር ያሟሸው እዚያው ነው።

ክራር አያሌ የምሽት መዝናኛ ቤቶችና የሠርግ ቤቶች ማለፊያ ትውስታዎችን አፍርቶለታል። የሙዚቃ ሕይወቱንም ቃኝቷል።

ምንም አንኳ ወደ ሳክስፎን ቢሻገርም።

አባቱ ሳህሌ አበበም ማለፊያ የኪቦርድ ተጫዋች ቢሆኑም የክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ የጥበብ ሙያ መለያቸው ለመሆን የበቃው ግና በሳክስፎን ነበር።
Ethiopian Imperial Guard Orchestra .jpg
Ethiopian Imperial Guard (First Division) Orchestra. Credit: As.Abebe
ሳህሌ አበበ የአቢይ አባት ብቻ ሳይሆኑ አስተማሪም ነበሩ። የክራርም የሳክስፎንም።

አቢይ ሳህሌ አበበ በቀጣዩ ክፍል ግለ ታሪክ ወጉ በሰርከስ ኢትዮጵያ ክራር ተጫዋችነት ወደ አውስትራሊያ መጥቶ እንደምን ለሳክስፎን ተጫዋችነትና አዲሱን አልበሙን ለማውጣት እንደበቃ ይተርካል።

Share