ከመድረክ ወደ ዩኒቨርሲቲ የጥበብ ትምህርት ቤት መንበር
ቤቲ ጂ ለዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢና የመማሪያ ክፍሎች አዲስ አይደለችም።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና Université de L'IAE Poitier በአስተዳደር ትምህርት በጥምር ዲግሪዎች ተመርቃባቸዋለች።
በዩኒቨርሲቲ የመማርና ማስተማር የቀሰመቻቸውን ዕውቀቶች ሰጥቶ በመቀበል ለምዕራቡና ለአገረ ኢትዮጵያ ታጋራለች።
Hollywood After Dark
ስርጭቱ ከ45 አገራት በላይ በሚዳረሰው "Hollywood After Dark" የቴሌቪዥን ትዕይንት ላይ ቤቲን ጨምሮ 50 ያህል የዓለማችን ምርጥ አርቲስቶች የጥበብ ሥራዎችን ለታዳሚዎቻቸው የሚያቀርቡብት ዝግጅት አካልም ሆናለች።
በቅርቡ የአርትኦት ሥራው ተጠናቅቆ ለዕይታ ሲበቃ አድናቂዎቿም የቢቲን ሶስት የዘፈን ሉላዊ የጥብበ ፍሬዎቿን የሚያጣጥሙላት ወቅት ይሆናል።
ቤቲ ጂ እና ኤልያስና በሙዚቃና በሕትመት የሙያ መስኮቻቸው የየድርሻዎቻቸውን ቢወጡም የሙያ መሠረቶቻቸውን የገነቡት ኢትዮጵያን አማክለው ነውና ሕመሟ ዘልቆ ይሰማቸዋል፤ ሐሴቷን ዘወትር ይመኛሉ።
የዘንድሮው የኢትዮጵያ 2016 የአዲስ ዓመት መልዕክታቸው ያተኮረውም እንዲያ ነው።
Betty, Lula, and Elias.
አሁን ያለው ሁኔታ እንኳን ኢትዮጵያዊ ሆኖ፤ ሰው ሆኖ የማያንገበግበው ዜጋ የለምኤልያስ ወንድሙ
የቤቲም ዕይታ ወደ ውስጣችን እንመልከት ነው።
'ጠላቱን የማያውቅ ወንድሙን ይገድላል እላለሁ' ችግራችን የሌላውን ቁስል አለማየት፤ በሌላው ጫማ ቆሞ መሔድ አለመቻል ይመስለኛልቤቲ ጂ
ኤልያስ የ2016 ተስፋና ስጋቱንም አክሏል።
- ተስፋ - ከስህተቶቻችን ተምረን፣ ድል ወራሽ ሆነን፣ በታሪካችን አዲስ ምዕራፍ ከፍተን፣ በኢትዮጵያዊነታችን ተከባብረንና ተዋድደን በጋራ ወደ ፊት የምንረማመድበት ወቅት።
- ስጋት - ፍራቻዬ እስክዛሬ ድረስ የሠራናቸውን ስህተቶችና ያሳለፍነውን መጥፎ ጊዜ በመርሳት እንዳንደግመው ነው።
ቤቲና ኤልያስ ለአገር፣ ለሕዝብና ለዓለም እንዳላቸው ተመሳሳይ የጋራ አተያየት ሁሉ፤ አንዳቸው የአንዳቸውን ሕይወት የሚጋሩትም በጥልቅ የፍቅርና መተሳሰብ ስሜት ነው።