አንኳሮች
- ውልደትና ዕድገት
- ከሙዚቃ ጋር ፍቅር ላይ መውደቅ
- ከክራር እስከ ፒያኖ
ግርማ ይፍራሸዋ ከክራር እስከ ፒያኖ፤ ከያሬድ እስከ ባኽ፣ ሞዛርትና ቢትሆቨን ግዘፍ ነስተው በአፍሪካ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ መድረኮች ላይ ናኝተዋል።
በመጪው ወርኅ ኖቬምበር በሜልበርን - አገረ አውስትራሊያ "The Spirit of the Nile" በሚል መጠሪያ ሶስት መድረኮች ተሰናድተውለታል።
Pianist Girma Yifrashewa. Credit: G.Yifrashewa
ግርማም መሰናዶውን ከውኖ ታዳሚዎቹን በምዕራባውያኑና አገርኛ ረቂቅ የፒያኖ ጥበብ ሥራዎቹ ከመድረክ እነሆኝ ለማለት ዝግጁ ሆኗል።