አንኳሮች
- የበጎ አድራጎት ተግባርና ሽልማት
- ድህነትና ሕፃናት በአገረ እንግሊዝ
- የቀድሞ ግብረ ሰናይ ተግባራትና የወደፊት የረድኤት ውጥኖች
አትሳቅ አትበሉኝ
ጭጋግ መሬት ቢረግጥ
ጸሃይ ብትሸፈን፣
አየሩ ቢታፈን፣
ኑሮ ረመጥ ቢሆን፣
ዙሪያው ገባው ሁሉ
ማቅ ለብሶ ቢዳፈን፡፡
ሳቄን ማን ከልክሎኝ፣
አልፎ ሂያጂነቴን
ጉዞዬን ማን ገቶኝ፣
እርቃኔንም ብሆን
የውስጤን ነጻነት እንደያዝኩት አለሁ
በውስጤ ሃብት አለኝ፡፡
አትሳቅ አትበሉኝ ... ሳቄ የቀረ ዕለት፣
የደኸየሁ እንደሁ ... በፈገግታ ንፍገት፣
ያኔ ነው የኔ ሞት፡፡
ጫማም አላቂ ነው
ከስር ተሸንቁሮ፣
ልብስም ይቀደዳል
ውሉ ተተርትሮ፣
ሁሉም አላፊ ነው
ያረጃል ያፈጃል
ትናንትም አርጅቶ
ጥንት ይባላል ዱሮ፡፡
አትሳቅ አትበሉኝ ... ሳቄ የቀረ ዕለት
የደኸየሁ አንደሁ ... በፈገግታ ንፍገት፣
ያኔ ነው የኔ ሞት፡፡
.............................
መታሰቢያነቱ ለጫማ አልባው ብላቴና ይሁንልኝ ... ጸደይ 2020
ምንተስኖት መንገሻ
ተጨማሪ ያንብቡ
አትሳቅ አትበሉኝ - በምንተስኖት መንገሻ