"የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድ ግብ ጠባቂ ለማ ክብረት ወገን አለኝ እንዲል፤ላበረከተው አገልግሎት ተሰባስበን እናመስግነው"ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውና አቶ ኤርሚያስ ወንድሙ

Ermias Tesfaye and Lemma.png

Dr Tesfaye Yigzaw, Vice President of the Ethiopian Community Association of Victoria (L), Lemma Kibret, former Ethiopian National Football Team goalkeeper (C) and Ermias Wondimu, former Ethiopian National Football Team player (R). Credit: Supplied

"ለማ ክብረት በዓለም ላይ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሊሰኝ የሚችል፤ ቅን፣ ሰው አክባሪና የታመመን ጠያቂ ነው" የሚሉት የቀድሞው የለማ ክብረት የብሔራዊ ቡድን ባልደረባ አቶ ኤርሚያስ ወንድሙና "ለሀገራቸው ያገለገሉ የማኅበረሰብ አባላትን ዕውቅንና ከበሬታ ልንቸራቸው ይገባል" የሚሉት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ቅዳሜ ሰኔ 1 / ጁን 8 በሜልበር ስለሚካሔደው የሕይወት ዘመን አገልግሎት ልዩ የዕውቅና ፕሮግራም ያስረዳሉ፤ የግብዣ ጥሪና ምስጋናም ለማኅበረሰብ አባላት ያስተላልፋሉ።


አንኳሮች
  • ኤርሚያስ ወንድሙና ለማ ክብረት ከክለን እስከ ብሔራዊ ቡድ ተጫዋችነት
  • ልባዊ ጓደኝነት፤ ከሀገር ቤት እስከ ስደት
  • የማኅበረሰባዊ ዕውቅናና ልገሳ ልዩ ዝግጅት

Share