አንኳሮች
- አዝማሪና የሙዚቃ ፍቅር
- ከሸክላ አድማጭነት ወደ መድረክ ባለቤትነት
- ከስደት ወደ አገር ቤት
አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሣ በ'የካቲት 12' ሆስፒታል ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ ትናንት ለሊት ሕይወቱ አልፏል።
ድምፃዊ ጌታቸው በ1960ዎቹ እና 1970ዎቹ በኢትዮጵያ በበርካታ ትላልቅ የሙዚቃ ክለቦች በመስራት ታዋቂነትን ማትረፍ ችሎ ነበር።
ጌታቸው ከሙዚቃ ሥራዎቹ ውስጥ "ብርቱካን ነሽ ሎሚ፣ ሀገሬን አትንኳት፣ ውብ አዲስ አበባ፣ ሳይሽ እሳሳለሁ፣ የከረመ ፍቅር" እና በሌሎች በርካታ ዘፈኖቹ ከፍ ያለ አድናቆትና ዕውቅናን አግኝቶባቸዋል።
አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ሙዚቃን ከ 6 አመቱ ጀምሮ የተጫወተ ሲሆን በፈጣን ባንድ ፣ ሸበሌ ባንድ ፣ የቬነስ ባንድ እና በኋላም ከዋልያስ ባንድ ጋር በመሆን የተለያዩ ይዘት ያላቸውን የሙዚቃ ስራዎችን ተጫውቷል።
ጌታቸው “ትዝታ እና ፈጣን” በሚባል የሙዚቃ ስልቶች ተወዳጅ የነበረ ሲሆን ከተጫወታቸው ተወዳጅ ዜማዎች መሃከል "ሀገሬን አትንኳት "፣ አዲስ አበባ" ፣ “ትዝ ባለኝ ግዜ”፣ "የከረመ ፍቅር” ፣ “መሄዴ ነው" ፣ "ሳይሽ እሳሳለሁ" የተሰኙት የሚጠቀሱ ናቸው።