“የምትሻገር አገር በማይሻገር ሐሳብ እየተናጠች ቆይታለች" ፕሬዚደንት ታዬ አፅቀሥላሴ

ሕወሓት አቶ ጌታቸው ረዳን ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ

President Taye.png

Ethiopia's new President, Taye Atske-Selassie. Credit: EBC

ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. የጋራ ስብሰባ በማድረግ ሥራቸውን የጀመሩት የፌዴሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች በተሰናባቿ ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ምትክ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴን በመሰየም ነው።

ጥምር ምክር ቤቱ አዲሱን ፕሬዚዳንት የሰየመው በአብላጫ ድምፅ ሲሆን፤ አምስት ድምፀ ተዓቅቦም ተመዝግቧል።

በመጀመሪያዪቱ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዚደንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ምትክ የተሾሙት ታዬ አፅቀሥላሴ ፕሬዚደንታዊ የሥራ ኃላፊነታቸውን ከተረከቡና ቃለ መሐላ ከፈፀሙ በኋላ ለጥምር ምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር "የሚታረቅና የሚታረም የፖለቲካ ልዩነት እንደማይታረቅ ተደርጎ በመሠራቱ አገር በማይጠራ የፖለቲካ ሳንካ እንድትንገላታ ተገድዳለች" ሲሉ ተናግረዋል።

 አያይዘውም “የምትሻገር አገር በማይሻገር ሐሳብ እየተናጠች ቆይታለች።"

"የፖለቲካ ወለምታዎችን ለማቅናት፤ ስብራቶችን ለመጠገን፤ ስንጥቃቶችን ለመድፈን ሲባል፣ ዛሬም ለነገ የታሪክ የቤት ሥራ ለማስቀመጥ የሚደረጉት ሙከራዎች የአገራችንን ፈተና አበርትተውታል" ብለዋል።

 ሕወሓት

 በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቡድን፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ አራት የካቢኔ አባላትን ጨምሮ 13 ኃላፊዎችን በተመሳሳይ መልኩ ከኃላፊነት ማውረዱን የገለጸው ቡድን፤ በምትኩ ተተኪ አመራሮችን መሾሙን ይፋ አድርጓል።


Share
Published 8 October 2024 9:41am
By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends