የመጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው ምርቶች እንዲወገዱ ከተደረጉበት ጉድጓድድ ቆፍረው በማውጣት ለመሸጥ በመዘጋጀት ላይ የነበሩ 17 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ድሬ ፖሊስ ገለፀ።
በከተማዋ ቀፊራ እየተባለ በሚጠራው የገበያ ስፍራ በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉና የአገልግሎት ግዜ ያለፈባቸው ምርቶች ከተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ ሱቆች 1ሺ700 ሊትር የምግብ ዘይት፣ ዱቄት ወተት እና ሩዝ ተለይቶ በመሰብሰብ በጉድጓድ ተቆፍሮ እንዲወገድ መደረጉን የገለፀው ፖሊስ ተከሳሾቹ ምርቱ ከተቀበረበት ጉድጓድ ቆፍረው በማውጣት ለመሸጥ በመዘጋጀት ላይ እንዳሉ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት መያዛቸውን አስታውቋል።
የአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያና የመጋላ ፖሊስ ጣቢያ በጋራ በሰሩት ቅንጅታዊ ስራ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው 10 ሴት እና 7 ወንድተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጧል።