እ.አ.አ በ1944 ፖላንዳዊው የሕግ ባለሙያ ራፋኤል ለምኪን፤ ለሆሎኮስትና ቀደም ሲል የተፈፀሙ ክስተቶችንም ባከለ ከፊል ምላሹ 'ዘር ማጥፋት'የሚል ቃል ፈጥረዋል።
የግሪክ ቅጥያ ቃልን ‘ጄኖስ’ ዘር እና የላቲን ቅጥያ ቃልን ‘ሳይድ’ ግድያ የሚለውን በማጣመር።
የጄኔቫው የዘር ማጥፋት ኮንቬንሽን በ1948 ለመፅደቅ የበቃው የለምኪንን የቅስቀሳ ዘመቻ ተከትሎ ነው።
በአሁኑ ወቅት ከ150 በላይ አገራት የኮንቬንሽኑ አካል ሆነዋል፤ ያም ማለት የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይደርስ ቅድመ መከላከል የማድረግ፤ ተፈፅሞም ሲገኝ የቅጣት እርምጃን የመውሰድ ኃላፊነት አለባቸው።
ይሁንና በዘር ማጥፋት ትርጓሜ ማዕቀፍ ውስጥ የሚካተቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ክስተቶችና ሁነቶች ቢኖሩም ሕጋዊ ዕውቅናን ማግኘት የቻሉት ግና እፍኝ የሆኑቱ ናቸው።
ለእዚህም አስባቡ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊና ሕጋዊ ጉዳዮች ናቸው።
እስካሁንም ድረስ 'ዘር ማጥፋት' የሚለውን ቃል በአብዛኛው ይሰማል፤ ከዓለም አቀፍ ሕግ ይዘት ጋር በተሰናሰለ መልኩም ባይሆን መጠነ ሰፊ ውድመትን አጉልቶ ከመግለጥ አኳያ።
በርካታ ጠበብት ቃሉ ሐዘንና ተቃውሞን ለመግለጥ ጥቅም ላይ እንደሚውል ይስማማሉ።
በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶችና ዓለም አቀፍ ሕግ ፕሮፌሰር ቫሱኪ ኔሲያህ “የተለያዩ ብርቱ በደሎችን መተርጎሚያ መንገድ ሆኗል" ይላሉ።