አከባበር፣ ምልሰታዊ ምልከታ፣ ሐዘን፤ የነባር ዜጎችና ፍልስተኞች የጃኑዋሪ 26 አተያይ

Untitled design (2).png

Andrew Gai, Maggie Ida Blanden and Commissioner Meena Singh share their perspectives on Australia Day. Credit: Supplied

የተወሰኑቱ የአውስትራሊያ ቀንን በአርበኛነት ስሜት ያከብሩታል፤ ሌሎች በፊናቸው በሐዘንና ተቃውሞ ያስቡታል። ጃኑዋሪ 26ን ተገቢ በሆነ መልኩ የማክበሪያ መንገዱ እንደምን ነው? ኢ-ፍትሐዊነትን ተፃርረው ቆመው ሳለ በሀገርዎ ላይ ኩራት ይሰማዎታልን?


አንድሩ ጋይ፤ እንደ አንድ አውስትራሊያዊ ለጥቂት ዓመታት የአውስትራሊያ ቀንን በኩራት አክብሯል።

የደቡብ ሱዳን ስደተኛ የነበረው አንድሩ ብሔራዊ ቀንን የማክበር ዕድል ስላልነበረው ተሳትፎው በታላቅ ኩራት የታጀበ ነበር።

ይሁንና፤ አንድሩ ሜልበርን ከሚገኙ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ማኅበረሰብ አባላት ጋር ወዳጅነቱን እያዳበረ ሲመጣ ጃኑዋሪ 26ን ማክበር ተገቢ የመሆኑን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ አስገባ።

“የአውስትራሊያ ቀን መቃረብና ካለፈም በኋላ ለነባር ዜጎች ሰቆቃን አስታዋሽ ነው፤ እናም ከእዚያ የተሻለ ነገር ማድረግ እንችላለን" ብሏል።
አንድ ቀን ሁሉም አውስትራሊያውያን፣ ከየትም ይምጡ ከየት፤ የሁሉም የደስታ ቀን ሆኖ የሚሰማቸው ዕለት ቢኖራቸው እወዳለሁ።
በየዓመቱ ጃኑዋሪ 26 በመጣ ቁጥር ማጊ ብላንደንና ሌሎች የፓላዋ ማኅበረሰብ አባላት በሆባርት የንግድ ማዕከል ከተማ ኤልሳቤጥ ጎዳና ላይ የቀድሞ አባቶችና እናቶች በፍልሚያ መስመር በአመፅ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ለመዘከር፤ በዘለቄታም ቅኝ አገዛዝ እስካሁን ድረስ ያለውን ተፅዕኖ አስመልክተው የተቃውሞ ሰልፍ ያካሂዳሉ።

ከተመልካቾች በእሷና ቤተሰባቸው ላይ የተሰነዘረባቸውንና የተቋቋሙትን ጎንታይ ነቀፌታ ታስታውሳለች።

"ሰዎች ጎዳና ላይ በተርታ ቆመው ጎንታይ ነቀፌታቸውን በጩኸት ይሰነዝሩብናል፤ ይሁንና አሁን እንዲያ መሆኑ ቀርቷል . . . ዓመታቱን በሙሉ በርካታ ሰዎች ከእኛ ጋር መቀላቀል ሲጀምሩ ተመልክተናል። ከእኛ ጋር ጎን ለጎን የሚጓዙ አጋሮችን አፍርተናል" ስትል ተናግራለች።
የአውስትራሊያ ቀን ክርክር ግሎ ባለበት ወቅት፤ ማጊ እና አንድሩ የመሸጋገሪያ መንገዱ ርህራሄና ተግባቦት እንደሁ ያምናሉ።

አንድሩ "ሰዎች ወጣ ብለው የእኛ ነባር ዜጎች ያላቸውን ውብ ባሕልና ደግነት እንዲያውቁ አበረታታለሁ"

"ያንንም በማድረግ መጪው ጊዜ፣ እንደ የአውስትራሊያ ቀን ያሉትም ለሁላችን ምን ማለት እንደሁ ይበልጡን ግንዛቤ ለመጨበጥ እንበቃለን" ሲል፤

ማጊም በማከል "አንዴ በጋራ አብረን መቆም ስንጀምር፣ ቁጭ ብለን አንዳችን ከአንዳችን እንማራለን፤ ታላቅ ሽርካዎችም ለመሆን እንበቃለን" ብላለች።

ይህ ክፍለ ዝግጅት፤ ጃኑዋሪ 26ን ለማክበር ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው? ኢ-ፍትሐዊነትን እያወገዙ ሀገረ አውስትራሊያ ላይ ኩራት ይኖርዎታልን? ሲል ጠያቂ ነው።

Share