የቁማር ድርጅቶች ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ማኅበረሰባትን ዒላማቸው አድርገዋልን?

"Pokies" - Gambling in Australia

Problem gambling rates in the Australian Chinese community are between two to eight times higher than the general population. Source: Getty / picture alliance

አውስትራሊያውያን በዓመት በቁማር 32 ቢሊየን ዶላር ያጣሉ፤ በግለሰብ ደረጃ ከማናቸው አገር በበለጠ። በተለየ ሁኔታም ዝንቅ ማኅበረሰባቱ ላይ ጉዳትን እያስከተለ ነው።


የቻይናውያን አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ፖል ፋንግ ከቁማር ጋር የተዋወቀው ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሳለ ነው።

“ለአዋቂዎች የማህጆንግ ወይም ካርታ መጫወቻ ጠረጴዛ አለ፤ እንዲሁም ለልጆች የማህጆንግ ወይም ካርታ መጫወቻ ጠረጴዛ አለ። ዝንጀሮ ያየውን ያደርጋል ዓይነት ነው (አሠራሩን ሳይገነዘቡና ለመዘዞቹም ስጋት ሳያሳድሩ)” ሲል ለSBS Examines ተናግሯል።

ፖል ቁማርን በየዕለቱ መቆመር የጀመረው ገና ለአካለ መጠን ሳይበቃ ነው።

“የአሸናፊነት ስሜት፣ ለስኬት መብቃትና ገንዘብ ማግኘት።”

እርዳታ ለመሻት የበቃው በ10 ቀናት ውስጥ አንድ ሚሊየን ዶላር ቆምሮ ከተበላ በኋላ ነው።

አሁን በማገገም ላይ ያለው ፖል ለSBS Examines ሲናገር ባሕል ምን ያህል ከቁማር ጋር ለነበረው ግንኙነት ሚና እንዳለው አመላክቷል።

“ቁማር በበርካታ ቻይናውያን ወይም እስያውያን ቤተሰብ ሥርዓት ዘንድ በእጅጉ አዘቦታዊነትን ተላብሷል” ይላል።

በአውስትራሊያ የቤተሰብ ጥናት መካነ ተቋም ገለጣ መሠረት የቻይናውያን ማኅበረሰብ የሱስ ቁመራ ደረጃ ከጠቅላላው ሕዝብ ከሁለት እስከ ስምንት እጅ እጥፍ የናረ ነው።

ከዝንቅ ቡድናቱም ውስጥ ተጋላጭ የሆነው የቻይናውያን ማኅበረሰብ ብቻም አይደለም።

የሲድኒ አካባቢ የጤና ባለሙያ ዋኢል ሳብሪ ለSBS Examines ሲናገሩ ዋነኛ ዓላማቸው የቁማር ጉዳትን በተመለከተ የሃፍረትና መገለልን አዙሪት ለመስበር መሻት ነው።

“ እንደ እውነቱ ከሆነ 'እኔ ክሽፈት ነኝ' ብሎ አለማለት እጅጉን ጠቃሚ ነው”

“አንስተን ልንነጋገርበት ያሻል። ድጋፍና ፍቅርንም ልንሰጣቸው ይገባናል” ይላሉ።

ይህ የSBS Examines ተከታታይ ዝግጅት ቁመራ እንደምን የአውስትራሊያ ዝንቅ ማኅበረሰባትን እየጎዳ እንዳለ የሚመለከት ነው።

እርስዎ ወይም ዘመድ አዝማድዎ ድጋፍ ካሹ፤ የቁመራ እርዳታ መስመር ላይ በ1800 858 858 ይደውሉ።

Share