የነባር ዜጎች ቱሪዝም ተፅዕኖዎች

Karrke Aboriginal Cultural Tour, Watarrka, NT

Karrke Aboriginal Cultural Tour, Watarrka, NT Credit: Archie Sartracom /Tourism Australia

እውነተኛ የሆነ አይረሴ የአውስትራሊያ ጉዞ ለማድረግ ይሻሉን? በሰዎች እምብዛም ያልተነካ፣ ምግብ፣ ሥነ ጥበብ ወይም ቅንጦት ይሁን፤ ከእዚህች ምድር ጋር የ 65,000 ዓመታት ቁርኝት ያላቸው አያሌ ሊጎበኟቸው የሚችሉ ልብ ሰቃይ የነባር ዜጎች ቱሪዝም አለ። ለተሞክሮዎ ጥልቀትን ማላበስ ብቻ ሳይሆን፤ የነባር ዜጎች ባሕላዊና ምጣኔ ሃብታዊ መልካም ዕድሎችን በመዘወርም እገዛዎን ያበረክታሉ።


ቱሪዝም አውስትራሊያ ተጓዦች ክልስና ብርዝ ያልሆነ የነባር ዜጎች ቱሪዝም መሳጭ ባሕላዊ ተሞክሮዎች ላይ ያላቸው ፍላጎት እያደገ መምጣትን ልብ ብሏል።

የነባር ዜጎች ቱሪዝምን በሕብር የሚያስተዋውቀው የአውስትራሊያ ቱሪዝም Discover Aboriginal Experiences (DAE) ዋና መኮንን የሆኑት ኒኮል ሚችል በርካታ ቱሪስቶች ስለ ነባር ዜጎችና አገራቸው ይበልጥ ማወቅን እንደሚሹ ያመላክታሉ።

“በ 2023 የዘመን መቁጠሪያ ወቅት አውስትራሊያን ይጎበኙ የነበሩ 969,000 ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች በነባር ዜጎች ቱሪዝም ተሳትፈዋል።”

“እንዲሁም፤ ደስታን በሚያሳድር መልኩ ከ 2019 እስከ 2023 የሀገር ውስጥ ተጓዦች ቁጥር በ22 ፐርሰንት ከፍ ብሏል። እናም፤ 1.185 ሚሊየን የአገር ውስጥ ጎብኚዎች የነባር ዜጎች ቱሪዝም ተሞክሮዎችን አግኝተዋል” ብለዋል።

እያንዳንዱ የጋራ DAE ጉብኝት የሚካሔደው በአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ሰዎች ነው።
Jarramali Rock Art Tour
Jarramali Rock Art Tour Credit: The Edit Suite/Tourism Australia

የታሪክ ባለቤትነት፤ ታሪክ ተራኪነት

የኩኩ ያላንጂ ሰው ሁዋን ዎከር የጥሻ ጉዞ ባሕል ተሞክሮዎችን በሩቃማው ሰሜን ኩዊንስላንድ ይመራሉ።

“ስለ ነባር ዜጎች ባሕል ለማወቅና ስለሚጓዙበት የብስና ባሕር እውነተኛ ግንዛቤን ለመጨበጥ የሚሹ ከሆነ ማለፊያው የመማሪያ መንገድ ከነባር ዜጎች የነባር ዜጎች ወገንን ታሪክ መረዳት ነው ብዬ አስባለሁ” ብለዋል
ገና ከጅማሮው እኒህ አካባቢዎች ለያዙት ጥንታዊ ሕይወት ካላቸው ባሕሎች ከመማር የላቀ መንገድ የለም።
ሁዋን ዎከር፤ የጥሻ ጉዞ ባሕል ተሞክሮች
አቶ ዎከር ጎብኚዎችን ፖርት ዳግላስ አቅራቢያ ስላለውና ድንቅ ስለሆነው የ135 ሚሊየን ዓመታት ዳያንትሪ የዝናብ ደን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይወስዷቸዋል።

ስለ ተለያዩ ሥነ ምሕዳር፣ ታሪክ ልማዶችና የተፈጥሮ ሃብቶች ያላቸውን ዕውቀት ለተጓዦች ያጋራሉ፤ እንዲሁም የአካባቢውን የደን ምግቦች እንዲቀምሱ ያበረታታሉ።

ምግብ የመኖሪያ ቀዬን ለቱሪስቶች ለማስተዋወቅ አንዱ ዋና መንገድ ነው።

የደን ምግቦች ልዩ ጣዕምና አጠቃቀሞች ዕውቅና ከፍ እያለ ባለበት ወቅት የነባር ዜጎችን ምግብ የመቅመስ ተሞክሮዎች ተመራጭ ከሆኑቱ የጉብኝት ዝርዝሮች ውስጥ የተካተተ ነው።
tourismAustraliaN.jpg
Tourism Australia recognises the growing interest in First Nations tourism as travellers seek out authentic and culturally immersive experiences.

የምድራዊ ገፅ ታሪኮቻችንን መግለጥ

የአውስትራሊያን አስደማሚ እምብዛም በሰዎች ያልተነኩ አካባቢዎች ለመቃኘት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንገዶች አሉ። የጀልባ ጉዞዎች፣ ውብ ተፈጥሯዊ ዕይታ የአየር በረራዎች ጉብኝቶችን ቅንጡ በሆነ ሁኔታ የማረፊያ ካምፕ ጋር የ 4WD ሳፋሪዎችን ያካታተቱ ይገኙባቸዋል።

ብሔራዊ ፓርኮቻችን በዓለም ጥቂት የሆኑ 20,000 ዓመታትን ያህል ዕድሜ ያስቆጠሩ የአለት ሥነ ስዕሎችን አቅፈው በመያዝ ሞገስን የተላበሱ ናቸው። የነባር ዜጎች የቱሪስት ምሪ እንዲህ ያሉ የተወሰኑ ባሕላዊ ዋጋ የተላበሱ አካባቢዎችን ይገልጣሉ።

የሰሜናዊው ግዛት ካካዱ ብሔራዊ ፓርክ በተፈጥሯዊና ባሕላዊ ዕሴቶቹ በዓለም የቅርስ መዝገብ ውስጥ የሠፈረ ሲሆን፤ በእጅጉ የአለት ሥነ ስዕል ከተከማቹባቸው ሥፍራዎችም አንዱ ነው።

ከፏፏቴዎቹ፣ የባሕር ዳርቻዎቹ፣ የዱር እንሰሳቱና የመዋኛ ሸለቆዎቹ ጋር የምዕራብ አውስትራሊያው ኪምበርሊ እንዲሁ ድንቅ የሆኑ የአለት ሥነ ስዕሎች ስብስብ መኖሪያ ነው።

እንዲሁም፤ አርኪዮሎጂና ምድረ በዳ በሚገጥሙበት የደቡብ-ምዕራብ ኒው ሳውዝ ዌልስ ሙንጎ ብሔራዊ ፓርክ በዓለም ቅርስነት ተመዘግቦ ይገኛል።

ጥንታዊ ደረቅ ተፋሰስ፣ ሙንጎ ሐይቅ በዓለም ላይ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የአርኪኦሎጂ ሥፍራዎች አንዱ ነው። ቅኝት፣ ካምፕ ማድረግ ወይም የጉብኝት መሪን መቀላቀል ይችላሉ።

ባሕላዊ መሳጭ ተሞክሮዎች

ወ/ሮ ሚችል፤ ተጓዦች ብዙውን ጊዜ በቀጥታ በሚሳተፉባቸው የግብራዊ ተሳትፎ ችሮታዎች እንደሚመሰጡ ይናገራሉ።
የሥነ ስዕል የትምህርት ክፍለ ጊዜን መከወን ወይም ከሲድኒ በስተሰሜን በሚገኘው ዋራሚ አካባቢ ባለው የአሸዋ ክምር ላይ ባለ አራት እግር የሞተር ብስክሌት ጀርባ ላይ ሆነው ስለ ባሕል መማር ይችላሉ።
ኒኮል ሚችል፤ የንባር ዜጎችን ተሞክሮዎች ይቃኙ ዋና መኮንን
እያንዳንዱ ለአገሪቱ ሕይወትን የሚዘራውና በአስደናቂው የነባር ዜጎች ምሪ የታጀበው ሁነት ለዘላለሙ ይዘዋቸው የሚቆዩትን አይረሴ ትዝታዎች ያፈሩልዎታል።
ggca-experiences-signature-aboriginal-experience-1.jpg
Great Golf Courses of Australia aboriginal experience

የአካባቢ ማኅበረሰባት ከቱሪዝም ትሩፋቶች ይቋደሳሉ

በነባር ዜጎች የሚመራው ቱሪዝም ለአካባቢው ማኅበረሰቦች ገቢ ከማስገኘቱም በላይ ባሕላዊ ዘላቂነትን ይደግፋል።

ማሩኩ ሥነ ጥበብ በማዕከላዊ አውስትራሊያ 900 ከሩቅ ነዋሪ ማኅበረሰቦች የተውጣጡ አርቲስቶችን ያቀፈ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች ጥበባቸውን እየሸጡ፣ ሆርሻዎችንና ባሕላዊ ጉብኝቶችን እያስተናገዱና በጥንታዊው የበረሃ መንገዶች እየተጋሩ በቀዬአቸው ሊቆዩ እንደሚችሉ ኒኮል ሚችል ያስረዳሉ።

ሚችል በዝነኛው የነጥብ ሥዕል አውደ ጥናቶች ላይ ተገኝተው ሲናገሩ “የሚከወኑት በአካባቢው በፒትጃንጃራ ቋንቋ በመሆኑ፤ ቋንቋውን ለመጠበቅም ይረዳል” ብለዋል።

ሁዋን ዎከር ባሕላዊ ጉብኝቶቹ ስለ ነባር ዜጎች ታሪክና ስለራሱ ቤተሰብ ታሪክ፣ ጎብኚዎች በቀዬው በሚቆዩባቸው ጊዜያት ለማስተማር እንዳስቻለው ይናገራል።

“ስለዚህ ለሥራ ርቆ ከመሔድ ይልቅ ከቤተሰቤ ጋር እንድቆይ አስችሎኛል፣ ከወገኖቼ ጋር እንድቀራረብ እና ከመሬቷ ጋር እንድቆራኝ ያበቃኛል። ለሰዎች ስለ ቅርሶቼ በማስተማርና ማጋራት መተዳደሪያን ማግኘት ትልቅ መንገድ ነው፤ በእርግጥም ሰዎች በጉብኝቶቻቸው ወቅት ለመሬት፣ ባሕርና የውኃ መውረጃዎች ትልቅ ከበሬታን እንዲቸሩ ማስቻል" ብለዋል።
Selfie Aboriginal Woman
As a First Nations Storyteller, Bundjalung man Kyle Ivey guides visitors on a climb of the Sydney Harbour Bridge as part of the Burrawa Aboriginal Climb Experience. Credit: davidf/Getty Images

ባሕል በከተማ ማዕከላት

የአገሬው ተወላጅ ባህል ራቅ ባሉ ቦታዎች ብቻ ሕልውና ያለው አድርጎ ግምት ማሳደር የተለመደነው፤ ግና በእኛ የከተማ ማዕከሎችም የበለፀጉ ታሪኮችን ታገኛላችሁ።

እንደ ነባር ዜጎች ታሪክ ተራኪነቱ፤ የባንድጃሉንጉ ሰው ካይል ኢቪ የሲድኒ ወደብ ድልድይ ላይ ሽቅብ ወጪ ጎብኚዎችንይመራል።

ሽቅብ የመውጣት ጉብኝቱን ለዕርቅ ሽቅብ መውጫነት ያህል ሊጠቀምበት እንደሚሞክርም ይናገራል።

“ድልድዩ ላይ በመራመድ እየወጣሁ ሳለ ቆም እልና ወጎችን ለማውጋት በቀለለ መልኩ ነገሮችን መዝዤ አመላክታለሁ”

ሽቅብ በመውጣቱ ወቅት አቶ ኢቪ ለአካባቢው ነባር ዜጎች ጠቃሚ የሆኑ ሁነኛ ጉዳዮችን ነቅሶ አመላክቷል። ቅድመ አያቶቹ በምድሪቱ ላይ እንደምን እንደኖሩና አውሮፓውያን ሠፋሪዎች ከመጡ ወዲህ ሲለወጥ መመልከታቸውን አጋርቷል።
ያገኘው ምንድን ነው፤ የኩራት መንፈስን ሲሆን፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን አውስትራሊያ ውስጥ ላሉ ከ500 በላይ ለሆኑቱ ዝንቅ ባሕላዊ ቡድኖችም ጭምር ነው።

“በተጨማሪም የማስታወስ ችሎታዬን እንደ አዲስ ለማቆየት ጥሩ መንገድ ነው። የበለጠ ወደፊት ለመግፋትና ጠልቆ ለማወቅ እንድሻ ያደርገኛል፤ በርካታ ወዳጆችን ለማካተትና ስሞችን እንዳላዛንፍ እርግጠኛ እንድሆን። በጣሙን አርኪ ተሞክሮ ነው” ብሏል።

መሃል ሜልበርን ውስጥ የነባር ዜጎችን ትክል የሥነ ጥበብ ለመመልከት በያራ ወንዝ ዙሪያ በአስጎብኚ ምሪ የሚካሔደውን የቢራራንግ ዊላም የእግር ጉዞ መቀላቀል ይችላሉ።

በጊዜ ብዛት ምድሪቱ እንደምን እንደተለወጠች ይሰማሉ። ለአካባቢው የኩሊን ሰዎች መሰባሰቢያነት እጅጉን ወሳኝ ነው።

ሌላው ሜልበርን ውስጥ የሚቸር የነባር ዜጎች ቱሪዝም ነው። አንድ ጉዞ በያራ ዙሪይ እንዲሁም ጉዞ በፊትዝሮይ ይገኛሉ።

ታዝማኒያ ውስጥ ኒፓሉና/ሆባርት በነባር ዜጎች የሚመራ የጉብኝት ተሞክሮን መከወን ይችላሉ። የ90 ደቂቃ የእግር ጉዞውና ትወና የአካባቢውን ፓላዋ ሰዎች የጨለማና አዋኪ ታሪክ ይነገርበታል።
A tour guide walked through the safety precautions of hiking into Kata Tjuta near a tent
Petermann, Northern Territoty / Australia - December 8, 2019: A tour guide walked through the safety precautions of hiking into Kata Tjuta near a tent Credit: alanlim97/Getty Images

የነባር ዜጎች ቱሪዝም ወደ ዕርቅ ይመራል

ኒኮል ሚችል እንዲህ ያሉ በነባር ዜጎች የሚመሩ ተሞክሮዎች ሁለቱም ነባር ዜጎች የሆኑቱና ያልሆኑቱ ባሕላዊ ዕውቀትን እንደሚጋሩበት ይገልጣሉ።

“እንዲሁም ለዕርቅ ሁነኛ ዘዋሪ ነው” ሲሉም አክለዋል።

“ሰዎች አውስትራሊያ ውስጥ ስላሉ የተለያዩ በርካታ ባሕሎች ዕውቀትን እየቀሰሙ ነው። እርስዎም ማኅበረሰባቱ ታሪካቸውን እንዲያጋሩ ግልፅ እየሆኑላቸው ነው። ከአስጎብኚዎቹ ውስጥ አንዱ 'ባሕልን ለመጠበቅ ባሕል ማጋራት አለብን' ሲል አንስቶልኛል” ብለዋል።

በተጨማሪም ይጎብኙ።

አዲሱን ሕይወትዎን አውስትራሊያ ውስጥ ስለ ማርጋት ጠቃሚ ምክሮችንና ፍንጮችን ለማግኘት የAustralia Explained ፖድካስት ደምበኛ ይሁኑ ወይም ይከተሉ።።

ማንኛውም ዓይነት ጥያቄዎች ውይም ርዕሰ ሃሳቦች አለዎት? ወደ ኢሜይል ይላኩልን።

Share