የግል የጤና ኢንሹራንስ ለመግባት ይሻሉን?

Doctor and patient in conversation in hospital hallway

Private health insurance (PHI) gives access to more comprehensive health services outside the public system. Credit: Solskin/Getty Images

አውስትራሊያውያን ጥራትና ለአቅም መጣኝ የሆነ የሕዝብ ጤና ክብካቤ ሥርዓት አላቸው። እንዲሁም፤ ሆስፒታሎችንና ስፔሻሊስቶችን ሲጎበኙ አጭር የቆይታ ጊዜን የሚያመቻችልዎና ተጨማሪ ምርጫዎች የሚፈቅድልዎ አማራጭ የግል የጤና ኢንሹራንስም አለ።


አንኳሮች
  • የግል ጤና ኢንሹራንስ የሕዝብ ጤና ሥርዓት ሸክምን ይቀንሳል
  • የግል ጤና ኢንሹራንስ ሽፋን ማለት የሆስፒታልና ስፔሽትያሊስት ተራ መጠበቂያ ጊዜያትን ያሳጥራል፤ እንዲሁም ለተወሰኑ የጤና አገልግሎቶች የወጪ ተመላሽ ያስገኛል
  • መንግሥት የግል ጤና ኢንሹራንስ ተጠቃሚነት ማነቃቂያ ድጎማዎችን ይቸራል
አውስትራሊያ የሕክምና ክብካቤና የሕዝብ ሆስፒታሎች ነፃ ወይም በአነስተኛ ወጪ የጤና አገልግሎቶችን መስጠትን ጨምሮ ከዓለም ምርጥ የሕዝብ ጤና ክብካቤ ሥርዓት ካሏቸው አገራት አንዷ ናት።

ይሁንና፤ አልፎ አልፎ አስፈላጊ አገልግሎቶችን አሟልቶ ለማቅረብ እክል ስለሚገጥመው፤ ከግል የጤና ሥርዓቱ ጋር ተደጋግፎ ይሠራል።

በፊሊንደርስ ኢንሹራንስ ተጠባቢ (አንፃፃሪ ድረገፅ) የሆኑት ቲም በኔት፤ ሜዲኬይር እንድንኖር አስችሎናል፤ ይሁንና ሁሉንም ለመሸፈን ትግል ገጥሞት እንዳለ ሲናገሩ፤

“የግል ኢንሹራንሱ ለማድረግ እየጣረ ያለው ምንድነው፤ አቅም ያላቸው ሰዎችን በማስገባት የተወሰኑ የሜዲኬይር ሸክሞችን ማቃለል ነው” ብለዋል።

ከሕዝብ የጤና ሥርዓት ውጪ፤ የግል ጤና ኢንሹራንስ እንደ ጥርስ ሥራ፣ የዓይን ክብካቤ፣ አካላዊ ሕክምናና አምቡላንስን የመሳሰሉትን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ የክፍያ አገልግሎትችን የሚሰጥ ነው።
Close up of man filling in medical insurance form
There are no gap fees if you’re treated in a public hospital; however, you might encounter additional expenses on your bill. Source: iStockphoto / mediaphotos/Getty Images

‘ሆስፒታል’ እና ‘ተጨማሪዎች’ ምንድን ናቸው?

እንደ አንድ የግል ታካሚ ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ለመታከሚያ የሚውል ወጪ ይሸፈናል። ለምሳሌ ያህል፤ የግል የጤና ክብካቤ ሽፋን ስር የእራስዎን ቀዶ ሕክምና ሐኪምና የኦፕራስዮን ቀንዎን መምረጥ ይችላሉ።

የተጨማሪዎች ሽፋን እንደ ጥርስ፣ የአካል ሕክምናና የዓይን ሕክምና የመሳሰሉ ሌሎች የጤና አገልግሎትችን ይሸፍናል። በሕግ የጠቅላላ ሐኪም ምርመራን ወይም የምስልና ከሆስፒታል ውጪ ምርመራዎችን አይሸፍንም።

የሆስፒታልና ተጨማሪዎች ሽፋንን በተናጠል ወይም ከሁሉን አቀፍ የኢንሹራንስ ጥቅል ጋር አብሮ መግዛት ይችላል።

የአውስትራሊያ ጎብኚዎችና የተወሰነ ቪዛ ባለቤቶች የባሕር ማዶ ጎብኚዎች ጤና ሽፋን መግዛት ይኖርባቸዋል።

የአውስትራሊያ የግል ጤና ክብካቤ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ ዶ/ር ራቼል ዴቪድ፤ አንዴ ቋሚ ነዋሪ ከሆኑ በኋላ ሜዲኬይርን ብቻ ተገን ሊያደርጉ ይችላሉ። ይሁንና፤ ቋሚ ነዋሪዎች በተለይም በባለሙያ ፍልሰተኞች ደረጃ ከግል ጤና ኢንሹራንስ ጋር መቀጠል እንደሚሹ ይገልጣሉ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሕዝብ ሆስፒታል ሥርዓት ላይ እጅግ የበዛ ውጥረት ለማሳደር አስተዋፅዖ አድርጓል።

ዶ/ር ዴቪድ “በወቅቱ ወይም በዕቅድ የሚካሔድ ቀዶ ሕክምና አሽቆልቁሏል”

“ፍልሰተኞች መጥተው የሚሠሯቸው አያሌ ሥራዎች ቀዶ ሕክምና ለማድረግ ለሳምንታት ከሥራ መቅረት የሚያስችሏቸው አይደሉም” ብለዋል።

የግል ጤና ክብካቤ ቀዶ ሕክምናና የአዕምሮ ጤና ክብካቤ ሕክምና በአጭር የቆይታ ጊዜ ለማድረግ ያስችላል፤ እናም በቂ የፋይናንስ አቅም ያላቸው ሰዎች የግል ጤና ሽፋን ለማግኘትተጨማሪ ይከፍላሉ።

ይህ በሕዝብ የጤና ሥርዓት ላይ ያለውን ጫና የሚያቃልል በመሆኑ፤ የኑሮ ትግል ላይ ላሉቱ የሕዝብ ጤና ክብካቤ አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል።

የሕዝብና የግል ሕሙማን የሚታከሙት በተለየ ሁኔታ ነው?

Senior woman at dental clinic for treatment
'Extras' covers additional specific health services such as dental, physiotherapy, and optical care. Credit: Luis Alvarez/Getty Images
የሕዝብ አሊያም የግል ጤና ሥርዓት ተጠቃሚ ይሁኑ፤ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የሚሠሩት በሥነ ምግባር መርሆዎች መሠረት ነው፣ የእርስዎ ክብካቤ ቀዳሚ ተግባራቸው ነው።

የግል ወይም የሕዝብ ጤና ሥርዓት ታካሚ በመሆንዎ በተለየ ሁኔታ አይታከሙም።

ማበረታቻዎች

መንግሥት የግል ጤና እንሹራንስ እንዲገቡ ሶስት ማበረታቻዎችን ይቸራል።

1. የግል ጤና ኢንሹራንስ ወጪ ተመላሽ

ይህ የመንግሥት አስተዋፅዖ አግባብ ያለው የግል ሆስፒታል ፖሊሲ ሽፋን ያላቸውን የፖሊስ ባለቤቶች ያግዛል። ዓላማው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን፤ በተለይም በጣሙን ውስብስ የጤና እገዛ የሚሹትን ለመርዳት ነው።

የወጪ ተመላሹ የኢንሹራንስ ፖሊሲው ወጪ 25 ፐርሰንት ሲሆን፤ ለእርስዎ የሚከፈለትዎትም በግብር ተመላሽ በኩል ነው።

ተመላሽ ለማግኘት ብቁ የሚሆኑት በፖሊሲዎ ዓይነት፣ ዕድሜዎና ገቢዎ መሠረት ይሆናል።

2. የሜዲኬይር ቀረጥ

የሜዲኬይር ቀረጥን የግል ጤና ኢንሹራንስ በመግባት ማስወገድ ይችላሉ።

ይህ ከፍተኛ ገቢ ኖሯቸው የግል ሆስፒታል ኢንሹራንስ ሽፋን በሌላቸው ላይ ተጣይ ታካይ ግብር መሆኑን ዶ/ር ዴቪድ ሲያስረዱ፤

“ማንኛውም የሥራ ገቢ ያለው ሰው የገቢ ግብር አካል የሆነውን የሜዲኬይር ቀረጥ ይከፍላል፤ ሆኖም የቤተሰብ ገቢያቸው በዓመት $183,000 ሆኖ የግል የጤና ኢንሹራንስ የሌላቸው ከሆነ ተጨማሪ የሜዲኬይር ቀረጥ ይጣልባቸዋል” ይላሉ።

የገቢ ገደቦችንና ቀረጦችን አስመልክቶ መረጃዎችን ይሰጣል።

3. የሕይወት ዘመን የጤና ሽፋን አጫጫን

ዕድሜያቸው ከ30 በላይ የሆነ የፖሊሲ ባለቤቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የጤና ኢንሹራንስ ሲገቡ በመጠኑ ከፍ ያለ የኢንሹራንስ ፖሊሲ ወጪ ያገኛቸዋል። ይህም አንድ በርካታ የጤና ችግሮች ያለበት የ85 ዓመት ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ የጤና ፖሊሲ ኢንሹራንስ ሲገባ ከአንድ የ25 ዓመት ሰው እኩል የጤና ኢንሹራንስ ፖሊስ ክፍያ እንዳይከፍል የሚያግድ መሆኑን ዶ/ር ዴቪድ ሲናገሩ፤

“ያ በወጣቶች ላይ ግዙፍ የፋይናንስ ጫና እንዳያስተላልፍባቸው ይገታል” ይላሉ።

የክፍተት ክፍያዎች ምንድን ናቸው?

‘የክፍተት ክፍያዎች’ ወይም ‘ከኪስ ወጪ’ ወጪዎች ሲባል ይሰማሉ። ይህም በእርስዎ የሕክምና ወጪና እርስዎ ባገኙት የጤና ኢንሹራንስ ተመላሽ መካከል ያለ ልዩነት ማለት ነው።

ከአንድ ጠቅላላ ሐኪም፣ ስፔሽያሊስት ወይም ሆስፒታል ሕክምና ሲያገኙ፤ አብዛኛው ወጪ በሜዲኬይር ወይም በእርስዎ የግል ጤና ኢንሹራንስ ይሸፈናል።

“በተጨማሪ የጤና ባለሙያ ወይም ሐኪም ክፍያ ያስከፍልዎታል፤ ለእዚያም ነው ያን ‘ክፍተት’ ብለው የሚጠሩት”

“ምክንያቱ ምንድነው፤ ሜዲኬይር ከዋጋ ግሽበት ጋር እኩል መራመድ አይቻለውም” በማለት ጠቅላላ ሐኪም ክሪስ ሞይ ያስረዳሉ።

በግል ታካሚነት ሆስፒታል ከተኙ፤ ልክ እንደ ማንኛውም ኢንሹራንስ ‘እላፊ’ ክፍያ ያክላሉ።
Full length, wide shot nurse fills in form with family sitting in hospital waiting room
By law, private health insurance (PHI) can’t pay for outpatient care such as a visit to the GP or imaging and tests outside hospital. Credit: PixelCatchers/Getty Images

ለእርስዎ ትክክለኛው የግል ጤና ኢንሹራንስ የትኛው ነው?

የጤና ኢንሹራንስን መምረጥ እርስዎ በሚሹትና ባለው አቅርቦት መካከል ሚዛን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው። ይህም ማለት በተቻለ መጠን የሚቻልዎትን መረጃ መሰብሰብ ይሆናል።

የኢንሹራንስ ፖሊሲ አንድን ሰውም ይሁን ወይም ቤተሰብን ሊሸፍኑት በሚፈልጉት ደረጃዎች ይወሰናል።

እናም በሒደት ፍላጎትዎ ሊለወጥ እንደሚችል ቲም ቤኔት ሲናገሩ፤

“አንዴ ኢንሹራንስ ስለ ገቡ ብቻ የተሻለ ዋጋ ማግኘትና አለማግኘትዎን በዓመት ወይም በሁለት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ ደግመው አያጣሩም ማለት አይደለም” ይላሉ።

አማራጮችን በመንግሥታዊው ድረገፅ በኩል ወይም እንደ , እና በመሳሰሉ አነፃፃሪ ድረገፆች አማካይነት ማስተያየት ይችላሉ።

Share