በሕዝበ ወሳኔ ዘመቻው ወቅት የታላካ እና ጉማትጁ ሰው ቾኖር ባውደን ድምፅ ለፓርላማ አስመልክቶ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ መጫን ጀመረ።
የተሳስተ መረጃን ጅረቶችን መፋለም ያዘ።
"ዕውቀትና በማስተላላፍና ማስተማር በመቻል ፈንታ ለሰዎች የተነገሩና የገጠመኙን የቅጥፈት ደንቃራዎች ማቃናት ያዝኩ" ሲል ገልጦታል።
በሕዝበ ውሳኔው ወቅት በአቦርጂናላ ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ላይ ዘረኝነት ናረ፤ የተወሰኑትም እዚህች ሀገር ውስጥ ያላቸውን ሥፍራ በተመለከተ እርግጠኞች እስካለመሆን ደርሰዋል።
"የሕዝበ ውሳኔው ውጤት በማኅበረሰቡ ውስጥ የመሰባሰብና ዘረኝነትን፣ የዘር ጥላቻንና ዘር ተኮር ስም ማጥፋትን በዘላቂነት ለመፋለም ከፊል የነፃነት ስሜትን ስሜትን አሳድሯል" ሲሉም የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት የማኅበራዊ ፍትህ ኮሚሽነር ካቲ ኪስ ተናግረዋል።
ይህ የ SBS Examines ተከታታይ ክፍለ ዝግጅት ክሽፈት ከገጠመው አንደኛ ዓመቱን ያስቆጠረውን የድምፅ ለፓርላማ ሕዝበ ውሳኔና የተሳሳተ መረጃም ለክሽፈቱ የነበረውን ሚና በምልሰት ቃኝቶ አንስቷል።