አውስትራሊያ ውስጥ ስውር የተቃውሞ መብትን ማሰስ

Australia Explained - The Right to Protest

SYDNEY, AUSTRALIA - SEPTEMBER 20: Young girls protest in The Domain ahead of a climate strike rally on September 20, 2019 in Sydney, Australia. Credit: Jenny Evans/Getty Images

በየሳምንቱ ስሜታቸው የገነፈለ አውስትራሊያውያን ጎዳናዎች ላይ ወጥተው ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን አንስተው ድምፆቻቸውን ያሰማሉ። ተቃውሞን ማሰማት ጥፋት አይደለም፤ ይሁንና አልፎ አልፎ ተቃዋሚዎች ፀረ ማኅበራዊና ፅንፈኛ በሆነ ሁኔታ የሕግን ወሰን ይጋፋሉ። እራስን ለችግር መዳረጉ እንደ ሥፍራውና እንደ አሳዩት ባሕሪይ ይወሰናል።


አውስትራሊያ ውስጥ ተቃውሞ የማሰማት መብት አለን የሚለው አመኔታ የጋራ ግንዛቤ ነው፤ ይሁንና ሕገ መንግሥታችን እንዲህ ያለውን መብት አላሰፈረም። ።

በምትኩ፤ በሕገ መንገሥቱ ስር ያለን መብት ፖለቲካዊ ዕሳቤያችንን የመግለፅ ነፃነት ነው።

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ዳኝነት ፋከልቲ ፕሮፌሰር ሉክ ማክናማራ “ለምሳሌ ያህል እንደ ቪክቶሪያ፣ የአውስትራሊያ መዲና ግዛትና ኩዊንስላንድ በመሳሰሉ ክልሎች ሃሳብን በሰላማዊ መንገድ ለመግለፅ የመሰብሰብ መብት በሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ውስጥ ዕውቅና ተሰጥቶታል”

“ይሁንና በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎችና በአገር አቀፍ ደረጃ በተለይ የተቃውሞ መብት አላችሁ የሚል የለም፤ እንዲያም ሆኖ ግና ዕሳቤውን በተለምዶ በእኛ የሕግ አካል የተቃውሞ መብትነት ተቀብለነዋል” ይላሉ።

አውስትራሊያ ውስጥ የተቃውሞ ሕጎች ይለያያሉ። ለምሳሌ ያህል፤ ኩዊንስላንድና ምዕራብ አውስትራሊያ ብርቱ ሕዝባዊ ትኩረትን የሚስቡ ግዙፍ የማዕድ ኢንዱስትሪዎች ስላሏቸው ጠንካራ የሆነ ፀረ-ተቃውሞ ድንጋጌዎች አሏቸው።

የፀረ-ተቃውሞ ሕጎች በጣሙን ግልፅ ያልሆኑ ሊሆኑም ይችላሉ።

ተቃውሞ ላይ በመታደም ሊከሰሱ ባይችሉም፤ ተቃውሞ በሚያካሂዱበት ወቅት ተቀባይነት የሌለው ባሕርይን ካሳዩ ግና ክስ ሊመሠረትብዎት ይችላል።
Australia Explained - The Right to Protest
TOPSHOT - Protestors march on the streets of Sydney's central business district against US President Donald Trump's travel ban policy on February 4, 2017. Source: AFP / SAEED KHAN/AFP via Getty Images

ተቀባይነት የሌለው ባሕርይ ተብሎ ግምት ውስጥ የሚገባው ምንድነው?

ሌሎችን የመጉዳትና ንብረቶች ላይ ጉዳቶችን የማድረስ ፀረ ማኅበራዊ ባሕሪያት በተቃውሞ ወቅት ተቀባይነት ያላቸው አይደሉም። ፕሮፌሰር ማክናማራ ተቀባይነት ያለው ባሕሪይ የቱ ነው ስለሚለው መጠይቅ ሲናገሩ፤

“ባሕርይ የሚገመገመው እንደ ጉዳዩ ነጠላ በነጠላ ነው። እናም ለምሳሌ ያህል፤ የአንድ የሠልፍ ተቃውሞ ወይም ቁጭ በማለት ወይም ራስን ከቁስ ጋር በማያያዝ የሚደረጉ የተቃውሞ እንስቃሴዎችን በሥፍራው ላይ ሆነው ለይተው የሚገመግሙት የፖሊስ ሠራዊት አባላት ናቸው” ይላሉ።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘመቻ አካሄጇ ኒኪታ ዋይት መፈክሮችን፣ ምስሎችንና ከተቃውሞው ጋር አብረው የሚሄዱ የስዕል ሥራዎችን መያዝ ተቀባይነት ያለው ነው፤ ሆኖም በመሳሪያነት ሊፈረጁ የሚችሉን ሳያካትት ሊሆን እንደሚገባ ሲያስረዱ፤

“ቢላዎች ወይም ተቀጣጣይ ነገሮችን በጭራሽ ይዘው ሊገኙ አይገባም” ብለዋል።

በተቃውሞ ወቅት አደናቃፊነት

በጎዳና ሠልፍ ወቅት ሁላችንም በአዘቦታዊ ክንዋኔዎቻችን ላይ መስተጓጎሎች ገጥመውናል። እኒህ ለመንግሥታት ትልቅ ጫና አሳዳሪ ሁነቶች በመሆናቸው አዲስ ገደቦችን ለመጣል እንዲጣደፉ ያደርጋል።

ፕሮፌሰር ማክናማራ፤ ለተቃውሞ መብት የምንቆም ከሆነ በሕይወታችን ውስጥ መጠነኛ የሆኑ መስተጓጎሎችን ልንቀበል ይገባል ይላሉ።
በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት መስተጓጎል ተፈጥሯዊ ነው ብሎ ማለት አግባብ ነው
ፕሮፌሰር ሉክ ማክናማራ፤ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ዳኝነት ፋከልቲ
“የሕዝባዊ ተቃውሞ አጠቃላይ ነጥብ ትኩረትን በመሳብ ሰዎች ቆም ብለው እንዲያስቡ፣ ምልስታዊ ምልከታ እንዲያደርጉና የሚተላለፍላቸውን መልዕክት በጥሞና እንዲያደምጡ ነው” ይላሉ።

ጉዳዩ ከፋፋይ ነው፤ እያንዳንዱ ክፍለ አገርና ግዛት መጠነ ሰፊ መስተጓጎልን በፈጠሩ ሰዎች ላይ ቅጣቶች ይጥላሉ።

ይሁንና በመላ አውስትራሊያ፤ እንደ ዋነኛ ወደብ፣ ጎዳና ወይም የግንድ ቆረጣ አካባቢ በመሳሰሉ ንግዶች ወይም ሰዎችን ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡ ማገድ በፀረ ተቃውሞ ሕጎች ስር ይካተታሉ።
Australia Explained - The Right to Protest
MELBOURNE, AUSTRALIA - AUGUST 21: A man holds a banner reading "Freedom" atop a tram stop during an anti-lockdown protest on August 21, 2021 in Melbourne, Australia. Credit: Getty Images
በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሳራ ሞዩልድስ፤ ሌሎችን ለማወክ ባይወጥኑም እንኳ እጅጉን ሁነኛ የሆኑ ጉዳዮች ሲሆኑ፤ እሥራትን ጨምሮ ብርቱ የሆኑ ቅጣቶች እንደሚያገኝዎት ሲያመላክቱ፤

“በአሁኑ ወቅት አደላይድ ውስጥ የሕዝብ ሥፍራዎችን ካደናቀፉ ለሶስት ወራት ለእሥር ሊዳረጉ ይችላሉ” ይላሉ።

አያይዘውም “ሕጉ ለትርጓሜ የሰፋ በመሆኑ የጎዳና ወይም ከሕንፃዎች ፊት ለፊት ወይም በፓርላማ የሚካሔዱ ተቃውሞዎች በእዚያ ሕግ ስር ይካተታሉ” ብለዋል።

አውስትራሊያ ውስጥ ያለ ፈቃድ የግል፣ የንግድ ወይም መንግሥታዊ አካባቢዎችን ዘልቆ ማለፍ፣ ጭምብል አጥልቆ ተቃውሞ ማካሔድ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ደራሽ ሠራተኛን ማደናቀፍ፣ የዛቻ ወይም ፀያፍ ንግግሮችን መጠቀም ወይም በንብረት ላይ ጉዳትን ማድረስ ሌላ መደበኛ ክሶችን የሚያስመሠርቱ ናቸው።

በገሃዱ ዓለም ግና በርካታ ሰዎች ለምሳሌ በሲቪል እምቢተኝነት፣ ሕንፃዎች ላይ ወጥተው በመስፈር ወይም መፈክሮችን ደልድይ ላይ በማንጠልጠል ሆን ብለው ሕግን በመጣስ ለእሥር ይዳረጋሉ።

ሕጎችን ማጠንከር

የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ባለፉት 20 ዓመታት ሕጎችን ለመለወጥ 34 ረቂቅ ድንጋጌዎች መቅረባቸውንና 26 ማለፋቸውን ሪፖርት አድርጓል። አብዛኛዎቹ ሕጎች ተቃውሞ ማድረግን አዋኪ እንዲሆን ያደረጉ ናቸው።

ዶ/ር ሞዩልደስ “ተቃውሞዎችን ወደ ወንጀል መለወጥ ተለማጅ እየሆነ ነው ማለት ይቻላል ብዬ አስባለሁ”

“ወንጀል የሚያደርጉት የድርጊት ዓይነት በተወሰነ ሥፍራ እየሆነም ይገኛል” ብለዋል።

ይሁንታን ማግኘት

አውስትራሊያ ውስጥ አስፈላጊው የተቃውሞ አካል ሕጋዊ ይሁንታን ማግኘት ነው።

ትልቅ የሆነ ሕዝባዊ ጉባኤ የሚያቅዱ ከሆነ፤ ለፖሊስ ወይም ለአካባቢው መንግሥት በመፃፍ ፈቃድ መጠየቅ ይችላሉ።

ፕሮፌሰር ማክናማራ “ያኔ ፖሊስ ተቃውሞዎን የማገድ እርምጃዎችን ከመውሰድ የሚገታ ይሆናል”

“ለምሳሌ ያህል፤ ይሁንታን ያገኘ ተቃውሞ ከሆነ ትራፊክን ለተወሰነ ሰዓት ማስተጓጎል፤ ለእዚያ ዓላማም መንገዶችን መዝጋት ወይም ቁጥጥር በሚደረግበት መልኩ ሠልፍን ማካሔድ ተፈቃጅነት ይኖረዋል” ብለዋል።

ፈቃዱ ፖሊስ ጣልቃ እንዳይገባ ወይም ሠልፈኞችን ወደ ጎን እንዳይል ጥቂት አመኔታን ይቸርዎታል። በምትኩም፤ የፖሊስ በሥፍራው መገኘት ተቃውሞዎቹ በተሳለጠ ሁኔታ እንዲከናወኑና ተቃዋሚዎቹም ጥበቃ የሚደረግላቸው ሆኖ እንዲሰማቸው ያደርጋል።

Australia Explained - The Right to Protest
SYDNEY, AUSTRALIA - MAY 06: Climate activists march through the CBD during the 'School Strike 4 Climate' on May 06, 2022 in Sydney, Australia. Credit: Lisa Maree Williams/Getty Images

በፖሊስ መታገት ቢገጥምዎትስ?

በፖሊስ ከታገዱ ጠበቃ ሊያናግሩ ይገባል። የማኅበረሰብ የሕግ ማዕከላት መብቶችዎ የተጠበቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሕጋዊ ምክሮችን ይለግሳሉ።

በርካታዎቹ ክሶች የጥቂት መቶ ዶላሮች መቀጮን ያስከትላሉ።
በመታደል ለእዚህ ነፃነት ዋጋ የሚሰጡ ፖሊስ፣ ዐቃቤ ሕጎችና ዳኞች ባሉበት ሕብረተሰብ ውስጥ እንኖራለን፤ እናም በእጅጉ የከፉ መቀጮዎች አልተጣሉም።
ዶ/ር ሳራ ሞዩልደስ፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር

መብትዎችዎን ይወቁ

በመላ አውስትራሊያ ተቃውሞና ሕግን በተመለከተ እንደ የ እና የአካባቢዎ ማዘጋጃ ቤት የሲቪል ነፃነቶች ያሉ ድርጅቶች ያልተዛባ መረጃን ይሰጡዎታል።

Share