የኩዊንስላንድ ነዋሪው ጆን የገንዘብ ችግር ከገጠማቸው በኋላ ኢሚግሬሽንና ከአንድ ሥፍራ ወደ ሌላ ሥፍራ ሔዶ መኖርን አስመልክቶ ባላቸው አተያይ መታወካቸውን ለ SBS Examines ሲያጋሩ፤
“ያደግኩት ሁሌም በመድብለ ባሕል ትሩፋቶች በተከበበ መሀል ከተማ ውስጥ ነው። ለእዚያም ነው አሁን የሚሰማኝ ስሜት የሚሰማኝ ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።
ገጠር አካባቢ መኖር ከጀመሩ ወዲህ ግና በሥራና ሽርሽር ቪዛ ከሚመጡት ጋር ለኪራይ ቤት ፉክክር ማድረግ እንደገጠማቸው ይናገራሉ።
“ለመፎካከር የሚያስችል ገንዘብ ከሌለህ፤ ዕድል ጀርባዋን ሰጠችህ ማለት ነው” ይላሉ።
እንዲህ በማሰቡ ረገድ ጆን ብቻቸውን አይደሉም።
የስካንሎን ተቋም ማኅበራዊ ትስስር ሠንጠረዥ በገንዘብ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች በበርካታ የመለኪያ መሥፈርቶች ዝቅተኛውን ነጥብ ይዘው ይገኛሉ።
“በአብዛኛው እራሳቸውን ሊያመላክቱ የሚያዘሙት በዝቅተኛ ተካታችነት ስሜት ነው፤ በመንግሥት ላይ ያላቸው አመኔታ ዝቅተኛ ነው፤ ሌሎች ሰዎች ላይ ያላቸው እምነትም ያነሰ ነው። እናም፤ በአብዛኛው ከሌሎች ተገልለው እንዳሉ ይሰማቸዋል" በማለት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አንቲያ ሃንኩክስ ይናገራሉ።
“እንዲሁም፤ ሕይወት አውስትራሊያ ውስጥ ከቶውንም የተሻለ አይሆንም ብለው ያስባሉ፤ እናም የፍልሰተኞች ተዛናቂነት አውስትራሊያን የሚያጠነክራት አይሆንም የሚል ስሜት ያድርባቸዋል” ሲሉም ያክላሉ።
በእኒህ በሃብት በልፅገውና የገንዘብ ችግር ጭንቀት ውስጥ ሆነው ባሉቱ መካከል እየሰፋ የመጣውን ክፍተት ልብ ያሉት የሲድኒ ሰሜናዊ ባሕር ዳርቻ የማኅበረሰብ መሪ የሆኑት ራቼል ሊያ ጃክሰን ሰዎችን ለማቀራረብ ይጥራሉ።
“አያሌ ድህነት፣ በርካታ መሟላትን ግድ የሚል ፍላጎትና መለያየቶች አሉ። ሰዎች ብቸኞች ናቸው፤ በበኩሌም እኔ ብቸኝነት ምን እንደሁ አውቃለለሁ።”
“መጨረሻው ግና፤ የማኅበረሰብ ጥንካሬ ማንነታችን ነውና አንድ ላይ ተሰባስበን፤ አንዳችን አንዳችንን መርዳት አለብን” ብለዋል።
ይህ የ SBS Examines ገቢር የኑሮ ውድነት ምን ያህል ማኅበረሰባችንን ለመከፋፈል ጫና እንዳለው የሚዳሥ ነው።