የፍልሰተኞች ቁጥር ለቤት ዋጋ ማሻቅብ አስባብ መስሎ ይታያል፤ ሆኖም የመስኩ ተጠባቢዎች በዋዛ እንዲያ መፈረጁ ቀላል እንዳልሆነ ይናገራሉ።
በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ጡረተኛ የሥነ ሕዝብ ፕሮፌሰር ፒተር ማክዶናልድ፤ አተያዩ ትኩረት ሳቢ ሊሆን እንደሚችል ለ SBS ሲያመላክቱ፤
"ፖለቲከኞችና አተያየት ሰንዛሪዎች የቤት ገበያ ማሻቀብን ከኢሚግሬሽን ጋር አያይዘው ሲገልጡ፤ የፖሊሲ መፍትሔ የሚሻውን የቤት ቀውስ ትኩረትን ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመላከቱ ነው"
"ይህ ቀውስ ነው፤ እናም በይፋ ሊነገር ይገባል። ይሁንና ሳቢያው ኢሚግሬሽን ስለሆነ፤ 'ኢሚግሬሽን ሲቀነስ፤ ችግሩ ይከላል' በማለት የሚከላ አይሆንም" ብለዋል።