"የአድዋ ጀግኖች ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉት ለእንጀራና ቡና አይደለም፤ የተለያየ ዘርና ሃይማኖት ላለው ሕዝብ ነፃነት ነው" ድምፃዊት ቤቲ ጂ

Betty G and Prince Ermias.jpg

Singer Betty G (L & C) and HIH Prince Ermias Sahle-Selassie, President of the Crown Council of Ethiopia. Credit: Supplied

"ሽልማት ማለት ሥራችሁን ጨርሳችኋል፤ አቁሙ ማለት አይደለም። ለኒሻን ሲሆን ደግሞ ለሀገር ገና ብዙ ትሠራላችሁ የሚል አደራም ጭምር ነው" የምትለዋ ድምፃዊት፣ የሰብዓዊ ረድዔትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ማንነት አጉሊ ድምፅ ብሩክታይት ጌታሁን "Betty G"፤ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት ስለተበረከተላት የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ኒሻንና ሀገራዊ አንድነት ፋይዳዎች ትናገራለች።


አንኳሮች
  • የኢትዮጵያ የክብ ኮከብ ኒሻን ሽልማት
  • የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት
  • የአድዋ ድልና የኢትዮጵያዊነት ፋይዳዎች

Share