ባልከው ዓለሙ፤ ከሰበታ መርሃ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት እስከ ቀለም ጉባኤና የሙዚቃ መድረክ

Arts and Entertainment

Singer Balkew Alemu. Source: Musikawi Production

ባልከው ዓለሙ፤ ማየት የተሳነው ድምፃዊና መምህር ነው። ከሰበታ መርሃ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት አንስቶ በውስጡ ያደረበትን የጋለ የሙዚቃ ስሜት ለስሙ መጠሪያነት መድረክ ላይ ለማዋልና የጥበብ ተሰጥዖውን ለማጋራት በብርቱ ታትሯል። በሙዚቃዊ የጉዞ ሕይወቱ ስለገጠሙት ተግዳሮችና ስኬቶች ያወጋል። ስለ መምህርነት ሙያውም ያነሳል። "ፈልጌ"ን ጨምሮ "የኔ ዓለም" በሚል የአልበም መጠሪያ ኤፕሪል 29 ወይም ሚያዝያ 21 ስለሚወጡት አዳዲስ ዘፈኖቹ ይናገራል። ለመላው ኢትዮጵያውያንም የበዓለ ፋሲካ መልካም ምኞቱንም ይገልጣል።



Share