የነባር ዜጎች የሥነ ፈለግ ጥናት፤ ሰማይ እንደምን ባሕላዊ ትግበራዎች ያመላክታል

Emu_Milky_Way.jpg

The celestial Emu in the Milky Way - Image Peter Lieverdink.

የሕዋ አካላዊ ቁሶች የነባር ዜጎች የሥነ ፈለግ ጥናት ዕውቀት ላይ ተፅዕኖን ያሳድራሉ፤ ሕይወትና ሕግንም ያመላክታሉ።


ብልጭ ድርግም በሚሉት ከዋክብት ጠለላና ኅልቆ መሥፈርት በሌለው የጨረቃ ዑደት ስር፤ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ባሕልና ሕላዌነት በሺህዎች የሚቆጠሩ ዓመታት የኋልዮሽ ምልሰተ ጉዞ ያደርጋል።

ከዕፁብ ድንቁ ፍኖተ ሐሊብ ጋላክሲ እስከ የሕዋ አናሳ ደንጊያዎችና የጨረቃ የተለያዩ ምዕራፎች፤ የሚቀሰሙ አያሌ የነባር ዜጎች ሥነ ፈለግ ጥናት ዕውቀቶች አሉ።

በምሽት ቀና ብለን ሰማይን ስንመለከት፤ ከዕለት ተዕለቱ ማለቂያ የለሹ የጨረቃ የፀሐይ ነፀብራቅ ምዕራፎች ጋር የተሰናሰሉ ውብ የከዋክብት ፍንጥቅ ጥቅሻዎችን እንመለከታለን።

ሥነ ፈለግ የአካላዊ ቁሶችና ክስተት ጥናት ነው፤ እናም የነባር ዜጎች ሥነ ፈለግ ከዋክብት ከምድር ጋር ያላቸው ቁርኝት ጥልቅ የዕውቀት ግንዛቤ ማናቸውም ምድር ላይ ያሉ ነገሮች የሰማይ ነፀብራቅ እንደሆኑ ያመላክታል።

ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች፤ የሰማይ ባሕላዊ ትግበራዎችን የማመላከት ምንጮች በሺህዎች ለሚቆጠሩ ትውልዶች የተላለፈው በታሪኮች፣ ዘፈኖችና ሥነ ስዕሎች አማካኝነት ነው።
pexels-eclipse-chasers-716719984-18285364.jpg
Moon over the Sydney Harbour Bridge – image Eclipse Chasers.
ሲድኒ የተወለዱት ያጋዲጋሏ ሴት አክስት ጆኧን ሰልፊ አስተዳደጋቸው የፍኖተ ሐሊብ ታሪኮችን ከእናታቸው፣ አረጋውያንና ማኅበረሰባቸው ውስጥ የመስኩ ዕውቀት ካላቸው ዐዋቂዎች ሲነገር እየሰሙ ነው።

“ከ 60,000 ዓመታት በላይ ነባር ዜጎች ወደ ሰማይ ተመልክተዋል። በዙሪያችን ያለውን ዓለም ለመረዳት ያግዛል። የከዋክብት፣ ፕላኔቶች፣ ጨረቃ፣ ፀሐይና ከባቢ አየር፣ የአየር ጠባይ ለውጥንና ወጀብን ለመተንበይ፣ በየብስና ውኃ ላይ ቅኝት ለማድረግ፣ እንዲሁም፤ የእህል ስብሰባ ዕቅድ ለመንደፍ፣ ለአደን፣ ንግድ ወይም ኩነትን ለመከወን፣ በተጨማሪም ታሪኮችን ለትውልድ ለማስተላለፍ” ሲሉ አክስት ጆኧን ያስረዳሉ።

አገር በቀል የከዋክብት ዕውቀት ለነባር ዜጎች ዓለማዊ አኗኗራቸውን፣ ሚናዎችና ኃላፊነቶችን የመገንዘቢያ መንገድ ነው።

አክስት ጆኧን “ማናቸውም አዚያ ሰማይ ላይ ያለ እዚህ ምድርም አለ – የሚል ይትባሃል አለን። እናም ማኅበረስብዎን፣ የዘፈን ስንኞችን፣ ጠቃሚ ሥነ ሥርዓት ማካሄጃ ሥፍራዎች፣ ከዋክብቶችን በመከተል የመንገድ አቅጣጫን መፈለግ ይቻላል። ይሁንና የእርስዎን ግንዛቤም ያሻል፤ ዳንስዎን፣ ቋንቋዎንና ከቀዬዎ ጋር ያለዎትን ቁርኝት ማወቁ ለሁሉም ነገሮች ይሁንታን ይቸራል” ይላሉ።

ዱዋን ሃማቸር በሜልበርን ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ቅርንጫፍ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። ከአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ማኅበረሰባት ጋር አብረው ይሠራሉ፤ ባሕላዊ ዕውቀቶችንም ይለዋወጣሉ።
አረጋውያኑ ማናቸውም ሰማይ ላያ ያለ ነገር ሁሉ ከምድር ጋር የተሳሰረ እንደሁ ይናገራሉ። እናም በዙሪያችን ያለው ዓለም እንደምን እንደሚሠራ ለመረዳት ካሹ፤ ከዋክብቶችን መመልከት ግድ ይልዎታል።
ዱዋን ሃማቸር
“ሰብዓዊ ፍጡራን ሁሌም ከሰማይ የተቆራኘ ግንኙነት አላቸው። ከዋክብቱ ሕዋንና ጊዜን እንድንረዳ ያግዙናል። ሕግንና ሳይንስን ያመላክታሉ። እንደ ፍኖተ ካርታና ክፍለ ጊዜም ያገለግላሉ። እንዲሁም፤ እንደ ብርቱ የትውስታ ቋት፣ ሰዎች ያልተበረዘ ዕውቀትን ለሺህ ዓመታት እንዲያስተላልፉ አግዘዋል” ሲሉ ዱዋን ሃማቸር ተናግረዋል።

ማናቸውም ሰማይ ላይ ያለ ነገር ትርጉምና ዓላማ አለው። የፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት እንቅስቃሴዎች በከባቢያችን እንደ ወቅቶች፣ የአየር ጠባይ ልማዶች፣ የተክሎችና እንሰሳት ባሕሪያትን ሲተነብዩ ቆይተዋል።
pexels-ken-cheung-3355734-5397911.jpg
The Australian sky at night - Image Ken Cheung.
ዱዋን ሃማቸር “የአገር በቀል የከዋክብት ዕውቀትን የመረዳት ሁነኛ ጠቀሜታ በዙሪያችን ካሉ ማናቸውም ነገሮች ጋር የተሳሰሩ መሆኑን ማወቁ ነው። ወቅቶች መቼ እንደሚፈራረቁ ለማወቅ ካሹ ሰማይን ይመልከቱ"

“መቼ እንደሚዘንብ፣ ማወቅ ከፈለጉ ሰማይን ይመልከቱ። የእንሰሳትን ወቅት የተከተለ ባህርያት መለየት ከወደዱ ወይም ተክሎች ወይም የጓሮ አትክልት መሰብሰቢያን ወይም ስለምግብ ምንጮች ማወቅ ካሹ ሰማይን ይመልከቱ። ከባቢዎ ምን እየነገርዎት እንደሁ ለመረዳት የሚፈልጉ ከሆነ ከዋክብትን እንደምን ማንበብ እንዳለብዎት ዕውቀት ሊቀስሙ ይገባል”

ይህ ሁለገብ ዓለምን የመመልከቻ መንገድ ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት የባሕል ማዕከል ነው።"

“ቶረስ መሽመጥ ውስጥ፤ አረጋውያን ከዋክብት እንደምን ብልጭ ድርግም እንደሚሉ ያስተምራሉ። ሊያነቧቸው የሚችሉ ከሆነ - ያም ማለት፤ እንደ ቀለማቸውን፣ ብሩህነታቸውን ወይም ምን ያህል ፈጣን በሆነ ሁኔታ ብልጭ ድርግም እንደሚሉ፣ መመልከትና መተርጎም መቻልን – ስለ ከባቢ አየር ጠቃሚ ነገሮችን ይማራሉ። ወጀብ ሊመጣ ስለመሆኑ ይነግርዎታል ወይም ከማዕዘን ማዕዘን የሚነፍሰው ንፋስ አቅጣጫውን ይቀይር እንደሁ ሊነግሩዎት ይችላሉ” በማለት ያስረዳሉ።

በየምሽቱ፤ ከዋክብት በምሥራቃዊ ሰማይ ከቀን ቀደም ብለው ይወጣሉ፤ በዓመቱ ውስጥ ምድር በፀሐይ ዛቢያ ዑደታዊ ዙር ስትከውን ከዋክብት ሙሉዕ ሆነው ይወጣሉ።

ይህ የሥፍራ ቅየራ ለውጥ ከምድር ዑደት ጋር ይገጣጠማል። እንደ አክስት ጆኧን አገላለጥ፤ ቅርፅዋ ሰማይ ላያ እንዳለው ኢሙ (አውስትራኢያ ውስጥ የምትገኝ ትልቋና በራሪ ያልሆነች የወፍ ዝርያ) ወይም በጨለማማ ፍኖተ ሐሊብ አካባቢ ሕብረ ከዋክብት በመባልም ይታወቃል።

“ስለ ሰማዩዋ ኢሙ የምወደው ምንድነው፤ ነባር ዜጎች ሰማይ ያሉ ጨለማማ ንጣፎችን እንደ ከዋክብት ያሉትን አክሎ እንደሚጠቀሙና ለሌሎች እንደምን እንደሚገልጡ ነው። እንዲሁም፤ ምክንያቱም በምድራዊ ኢሙ የምንመለከተው ባሕሪይ በተመሳሳዩም ከሰማይቱ ጋር በሰማይ ላይ ያለው መረጃ ተመሳሳይነት ያለው መሆን ነው” ሲሉ አክስት ጆኧን ይናገራሉ።
The Dark Emu rising - Image by Geoffrey Wyatt - Sydney Observatory.png
The Dark Emu rising - Image Geoffrey Wyatt.
ለምሳሌ ያህል፤ በኤፕሪልና ሜይ ከጀምበር ጥልቀት በኋላ ሰማይ ላይ ጥቁራማው ኢሙ ጎልቶ መታየት ሲጀምር፤ ከምድራዊው ኢሙ ጋር ተገጣጣሚ ክስተት አለው።

ዱዋን ሃማቸር “ይህ ግጥምጥሞሽ ኢሙዎች የሚራቡበት ዓመታዊ ጊዜ መሆኑ ነው።”

“ወራቶች እንዳለፉም ጥቁራማው ኢሙ ጁንና ጁላይ ግድም ከአናት በላይ ከፍ ይላል። በእዚያ ወቅት ወንድ ኢሙዎች ዕንቁላሎችን የሚታቀፉበት ጊዜ ነው። ወደ ድቡብ ምዕራባዊ አድማስ ቀጥ ብለው በሚዞሩበት ኦገስትና ሴፕተምበር ወቅት ላይ ጫጩቶች መፈልፈል ይጀምራሉ” ሲሉ ያስረዳሉ።

ምድራዊው ኢሙ፤ በትረካ ተላልፎ በነባር ዜጎች ልማዳዊው ታሪክ ውስጥ የሚጠቀሰው ጠቃሚ ሳይንሳዊ መረጃን ያካተተ ነው።

ዱዋን ሃማቸር “የደቡብ ቪክቶሪያ ጉኔይልኩራኒ አረጋዊ የጨረቃ ሰው እንደምን ኢሙን ያድን እንደነበር ይተርካሉ። ኢሙ ወንዝ ላይ ተንጋልሎ ወደ ነበረ አንድ ዛፍ በመሮጥ ለማምለጥ ሞከረ። ግና ተንሸራትቶ ወንዙ ውስጥ ወደቀ። ዛሬ ያን ምስል ሰማይ ላይ ታዩታላችሁ። የኢሙ ምስል በሰማይ ወንዝ ላይ - በፍኖተ ሐሊብ ወይም ዋራምቡል ላይ ተንጋልሎ”

“ወንዙ ላይ ተንጋልሎ ያለው የያራን ዛፍ ከኢሙ ራስ ጎን የሚገኘው ደቡባዊ መስቀል ነው። የጨረቃ ሰው ብቅ ሲል፤ ኢሙ ከአዳኙ ይሰወራል። ይህ ብሩሁ የጨረቃ ብርሃን ተፈጥሯዊ ብናኝ በንኖ ፍኖተ ሐሊብ ውስጥ በመጋረዱ ኢሙውን ለማየት እንደምን አዋኪ እንዳደረገው ነው” ሲሉ ተርከዋል።

እንደ ተወርዋሪ ኮከቦች ዓይነት በምሽት ሰማይ ላይ የሚከሰቱ ጊዜያዊ ክስተቶች በነባር ዜጎች ባሕል ዘንድ ትርጉም አላቸው።
2024-09-02_16-18-07.jpg
Aunty Joanne Selfe - Image supplied. Associate Professor Duane Hamacher, image – Amanda Fordyce.
እንደ ዱዋን ሃማቸር ገለጣ፤ አረጋውያን እኒህ ነገሮች ሕይወት፣ ሞትና ማንነትን ለመረዳት ጠቃሚ እንደሆኑ እንደሚያስተምሩ ሲያመላክቱ፤

“በአብዛኛው ሰሜናዊ አውስትራሊያ፤ ብሩህ ተወርዋሪ ኮከቦች የሰይጣን መንፈስ ጅማሮዎች ናቸው። ተወርዋሪ ኮከቦች በመላ ሰማይ ላይ የሚዘዋወሩ አካላት ተምሳሌዎች ናቸው። ቶረስ መሽመጥ ውስጥ፤ ብሩህ ተወርዋሪ ኮከቦች ሜየር ተብለው ይጠራሉ። ተምሳሌነታቸውም ሰማይ ላይ እንደሮኬት የሚወነጨፉ ምድር ላይ የሞቱ ሰዎች መንፈሶችን እንደሁ አረጋውያን ይናገራሉ” ሲሉ ሃማቸር ይጠቁማሉ።

በአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ዘንድ ከዋክብት ማንነትና ተጓዳኝነትን፣ የተፈጥሯዊ ዓለም አካልነትና ባሕልን አካትተው የያዙ ናቸው።
በነባር ዜጎች ሥነ ፈለግ፤ የአፅናፈ ሰማይ መነሻ የኋሊዮሽ እስከ ጁኩርፓ ድረስ ሔዶ ይመዘዛል። ምዕራባውያን ያንን ማለም ሲሉ ይጠሩታል፤ ይሁንና በጥንተ ጥንታዊ ዘመን የሁሉም ፍጡራን መነሻ መሠረት ነው።
አክስት ጆኧን
አክስት ጆኧን “ሆኖም፤ እንደ እኛ አረዳድ የእዚህ ታሪክ አስገራሚነት ጊዜም ሆነ ታሪክ ትርጓሜው እየተለወጠ መምጣትን ነው፤ ፅንሰ ሃሳብ አለን – ማለም እንለዋለን። መንፈሶች ምድርን እየዞሩ፤ ተራሮችን፣ ወንዝን፣ ሰማይን ማናቸውንም በዙሪያችን የምናያቸውን ምድራዊ ቁሶችን እንደሠሩ ሁሉ፤ በእርግጥም እኛ የምንኖርበት አፅናፈ ሰማይ ተባባሪ ፈጣሪዎች ስለመሆናችን የጨረፍታ ዕይታ የሚሰጠን ነው። ተመልካችና ታዪ አንድ ናቸው" ብለዋል።

በእዚህ መንገድ፤ አገር በቀል ዕውቀት ለነባር ዜጎች ያለፈውን፣ አሁነኛና መጪውን አቆራኝቶ የሚያዋድድ ማዕከል፤ ሁለገብ የዕውቀት ሥርዓት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ   እና ይጎብኙ።
Subscribe or follow the Australia Explained podcast for more valuable information and tips about settling into your new life in Australia.

Do you have any questions or topic ideas? Send us an email to

Share