የኤልያስ ዋንጫ፤ "ኤልያስ አገራችን ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ነው" አቤል አስመላሽ

Elias Juhar.jpg

Elias Juhar. Credit: Supplied

በአዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ "የኤልያስ ዋንጫ" በሚል ስያሜ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ የዘገበ ፊልም እሑድ ሚያዝያ 6 ከቀትር በኋላ በሜልበርን ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ቀርቧል። ዝነኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና ክለብ ተጫዋቾች በሥፍራው ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠዋል።


አንኳሮች
  • "የኤልያስ ዋንጫ" ፊልም ፋይዳ
  • የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች አስተያየት
  • "የኤልያስ ዋንጫ" ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅና ዳይሬክተር አተያይ

Share