የተሳሳተ - እና አሳሳች መረጃ — የሐሰት መረጃ፤ ሆን ብሎ ማሰራጨት ወይም ባለማወቅ ማጋራት ከፍተኛው ሉላዊ ስጋት ተብሎ በዓለም የምጣኔ ሃብት መድረክ ተሰይሟል።
ማኅበራዊ ሚዲያም ጉዳዩን አቅላይ አልሆነም።
የUncomfortable Conversations ቀራጭና አስተናጋጅ የሆነው ጆሽ ዚፕስ “እኛ በማኅበራዊ ሚዲያ የተቀረፀና መጠነ ሰፊ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ታክሎበት በድንገት የኑክሊየር መረጃ የተቸረን ስልጣኔ ነን — በእሳት ላይ ነዳጅ የመጨመር ያህል” ብለዋል።
የነፃ ንግግር ተሟጋቹ ሃሳቦችን በኦንላይን ማጋራቱ የተሳሳተ መረጃ ተደርጎ አሉታዊ ትርጓሜ ሊኖረው እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ይገልጣሉ።
“እውነታው፤ ግዙፍ፣ ዝንቅ፣ ብዝሃነት፣ መድብለ-ዘውግ ኅብረተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ... ከአያሌ ሃሳቦች ጋር መታገልን ግድ ይልዎታል፤ በተወሰነ የኅብረተሰብ ስብስብ ዘንድ ዘለፋ ወይም ስድብም ሆኖ ይወሰዳል።"
"የተወሰኑቱ በተሳሳተ መረጃና አሳሳች መረጃ መካከል ሊሆኑ ይችላሉ” ሲሉ ለSBS Examines ተናግረዋል።
ወደፊት ለመራመድ የተሳሳተ መረጃና አሳሳች መረጃ ውል ያለው ትርጓሜ እንደሚያሻው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ሎሬይን ፊንሌይ ልብ ሲያሰኙ፤
“ሁለቱንም ልንከውን ይገባል፤ ሰዎችን ከሐሰት መረጃ መጠበቅና እንዲሁም፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ለንግግር ነፃነትም ጥበቃ ስለማድረጋችን እርግጠኞች ልንሆን ይገባናል” she said.
ይህ የ SBS Examines ክፍል፤ የንግግር ነፃነትን ሳንገድብ የተሳሳተ መረጃን መፋለም እንችላለን? ሲል ይጠይቃል።