ረመዳንና ኢድ ምንድናቸው አውስትራሊያ ውስጥ የሚከበሩትስ እንደምን ነው?

Lantern With Moon Symbol And Mosque Shape Background. Ramadan Kareem And Islamic New Year Concept.

What are Ramadan and Eid and how are they celebrated in Australia?Play10:34 Credit: Songyuth Unkong / EyeEm/Getty Images

ሙስሊሞች አውስትራሊያ ውስጥና በመላው ዓለም ረመዳንን በማክበር ራሳቸውን ሰጥተው ለአንድ ወር ፆም በሚፆሙበት ወቅት የቅዱስ ወሩን ሃይማኖታዊ ትሩፋቶች እንቃኛለን።


አንኳሮች
  • ረመዳን በእስልምና ጤናማ ጎልማሳ ሙስሊሞች ከጎሕ መቅደድ እስከ ጀምበር ጥልቀት የሚፆሙበት ቅዱስ ወር ነው
  • ኢድ አል ፈጥር የቅዱሱ ወር የፆም ፍቺ ለሶስት ቀናት የሚከበርበት ነው
  • ሙስሊም አውስትራሊያውያን ለኢድ ክብረ በዓል ልዩ ባሕላዊ አከባበራቸውን ያዋድዱበታል
አውስትራሊያ አያሌ የሙስሊም ሰዎች የሚኖሩባት መድብለባሕል አገር ናት። ከተማ ወይም አንድ ትልቅ የመንደር ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ምናልባትም ከአንድ ሙስሊም ጋር አብረው ሠርተው ወይም ወዳጅ ሆነው ይሆናል።

የአንዱ የሌላውን ሃይማኖትና ባሕል መረዳትና አድናቆትን መቸር የመድብለባሕል ሕብረተሰብ ዝንቅነት መሠረት ነው።

ሙስሊሞች፤ አውስትራሊያን ጨምሮ በመላው ዓለም የቅዱስ ረመዳን ወርን ያከብራሉ። የእዚህ የወር ዕድሜ ያለው ቅዱስ ወር ግብረ አምልኮና ፆም በእስልምና እምነትና ባሕላቸው ውስጥ ሁነኛ ሥፍራ አለው።

Man praying in the sunset (Pixabay).jpg
The Islamic Hijri calendar, is based on the cycles of the moon around the Earth. Credit: Pixabay

እናም፤ ረመዳን ምንድን ነው?

ረመዳን ጤናማ ጎልማሳ ሙስሊሞች ከጎሕ ቅደት እስከ ጀምበር ጥልቀት መፆም የሚጠበቅባቸው፤ የእስላማዊ ጨረቃ ዘመን መቁጠሪያ ዘጠነኛ ወር ነው።

በረመዳን ውስጥ ሙስሊሞች ትልቅ ትምህርት የሚቀስሙበት፣ ራሳቸውን የሚያጎለብቱበትና በዲሲፕሊን የሚመሩብት ሂደት እንደሁ ይገልጣሉ።
ረመዳን ለሙስሊሞች በዓመቱ ውስጥ የተቀደሰ ወር ነው፤ እናም ያ የተለየ ወር ያደርገዋል።
ፕሮፌሰር ዙለይሃ ከስኪን፤ በሜልበርን ቻርልስ ስቱአርት ዩኒቨርስቲ የእስላማዊ ጥናቶችና ስልጣኔ ተባባሪ ኃላፊ
የሂጅራ ዘመን መቁጠሪያ በመባል የሚጠራው የአቆጣጠሩ መሠረት የጨረቃ ዑደት ነው።  

በመሆኑም፤ የእስላማዊ ኩነቶች ቀናት ይለያያሉ፤ እናም የዘመን መቁጠሪያው ከፀሐይ ዓመት ከ10 እስከ 12 ባሉ ቀናት ያጠረ ነው።  

ይህም ማለት በየዓመቱ የረመዳን መጀመሪያ ይለያያል።  
Fasting
A meal with loved ones during Ramadan Source: Getty / Getty Images Jasmin Merdan

ፆም ሙስሊሞችን ግድ የሚላቸው ስለምን ነው?

ፆም አምስት የእስልምና ምሰሶዎች ከሆኑት እምነትን መግለጥ (በአላህ ማመን) ሶላት፣ ዘካ፣ ፆም እና ሐጅ ማድረግ አንዱ ነው።

በተለይም በፆም ወቅት፤ ሙስሊሞች ሲጋራ ከማጤስ፣ ወሲባዊ ግንኙነቶችን ከመፈፀም፣ ቁጣን ከማሳየት ወይም ንትርኮችን ከማካሔድና ኢሞራል የሆኑ ድርጊቶችን ከመፈፀም መቆጠብን ግድ ይሰኛሉ።

ሙስሊሞች እንደ ፀሎት ማድረግን፣ ንባብን፣ ቁርዓንን መረዳትና የረድኤት ሥራን ጨምረው እንዲያከናወኑ ይበረታታሉ።

ፆማቸውን ከከወኑ በኋላ በርካታ ሙስሊሞች ለማድረግ መስጊድ ይገኛሉ።

ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ካቲም ላቺር፤ ረመዳን ከምግብና መጠጥ መቆጠብ በላይ መሆኑን ሲናገሩ፤

“ከሁሉም በላይ፤ የመንፈሳዊነት ወር ነው፤ በአንድ እምነት፣ ከአንድ እግዚአብሔር ጋር ዳግም መቆራኛ ወር ነው” ይላሉ።
ዳግም ሩህሩህ ሰብዓዊ ፍጡርነትን የምንማርበት፣ ለመመገብ አቅሙ የሌላቸው ድሆች የሚያስፈልጓቸውን የምንገነዘብበትና በዙሪያችን ካለው ዓለም ጋር የምንተሳሰርበት ወር ነው።
ፕሮፌሰር ካሪማ ላቺር፤ በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የአረብና እስልምና ጥናቶች ማዕከል ዳይሬከተር
በተጨማሪም፤ ፆም የፀሎትና ሃይማኖታዊ ግዴታን ከመወጣት በላይ የ እንዳሉት ሲያስረዱ፤

“አካላዊ በሆነ መልኩ በጣሙን ጤናማ ነው፤ ስለምን የሰውነትን ሜታቦሊዝም ያበጃል፤ ማናቸውንም ዓይነት መርዛማነት ያፀዳልናል። በጣሙን ጤናማ ሂደት መሆኑ የተረጋገጠለት ነው፤ እናም፤ ያልተቆራረጠ ፆም ምን ያህል ለሰውነት ጠቃሚ እንደሆነ እናውቃለን” ብለዋል።
Shot of a young muslim woman pouring drinks for her family
A meal with loved ones during Ramadan. Source: iStockphoto / PeopleImages/Getty Images/iStockphoto

ኢድ ምንድነው?

ሙስሊሞች የሙሉ ወሩን ፆም ሲፈቱ ኢድ ይሆናል።

ኢድ የሚለው ቃል በአረብኛ 'በዓል' ወይም 'ድግስ' ማለት ሲሆን፤ በእስልምና ዘመን መቁጠሪያ ሁለት ኢዶች አሉ፤ ኢድ-አልፈጥር እና ኢድ-አል አድሃ።

ኢድ አል-ፈጥር፤ እንደ 'አነስተኛ ኢድ' ሲታይ፤ የረመዳንን ወይም ፆምን ማብቃት አስመልክቶ ለሶስት ቀናት የሚከበር ክብረ በዓል ነው።

በሜልበርን የቻርልስ ስቱአርት ዩኒቨርሲቲ፤ የእስልምና ጥናቶችና ስልጣኔ ማዕከሉ ዶ/ር ዙለይሃ ከስኪን “ኢድ አል-ፈጥር በወርኅ ረመዳን የተገኘን ስኬት የማክበሪያ አጋጣሚ ነው" ይላሉ።

ኢድን ሲያፈጥሩም፤ ሙስሊሞች ዛካ አል-ፈጥር በመባል የሚታወቀውን ችሮታ እንዲቸሩ ግድ ይሰኛሉ፤ ድሆችም ማክበር እንዲችሉ።

ፕሮፌሰር ላቺር፤ ኢድ አል-ፈጥር “የአብሮነትና ይቅር ባይነት” ክብረ በዓል ነው። የማኅበረሰቡን መንፈስ እንደሚያድስ ሁሉ፤ ሙስሊሞች ይቅርታን እንዲጠይቁም ያበረታታል ባይ ናቸው።

በተጨማሪም፤ ልጆች የመደሰቻ ጊዜ እንዲኖራቸው፣ አዳዲስ ጓደኞችን እንዲያፈሩና ከባሕሉ ጋር እንዲላመዱም ትልቅ አጋጣሚን ይፈጥራል።

በተለይም ለልጆች አዳዲስ ልብሶችን መግዛት፣ ቤትን ማፅዳት፣ ልዩ ጣፋጮችንና ምግቦችን ማዘጋጀት የኢድ አንዱ ትልቅ አካል ነው።

እንዲሁም፤ 'የመስዋዕት ኢድ' ወይም ታላቁ ኢድ በመባል የሚታውቀው ኢድ አል-አድሃ ከዓመታዊው ሐጅ የሚከተልና አብርሃም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመፈፀም ልጁን ኢስማኢልን ለመስዋዕት በፈቃዱ ያቀረበበት ነው።
Tradicionalni muslimanski roditelji i njihova djeca dijele lepinju tokom iftara u Ramazanu
In most Islamic countries, Eid al-Fitr is a public holiday. Source: iStockphoto / Drazen Zigic/Getty Images/iStockphoto

ሙስሊም አውስትራሊያውያን ኢድን የሚያከብሩት እንደምን ነው?

የኢድ አከባበር ማለዳ ላይ በልዩ ፀሎት ይጀመራል። በበርካታ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ አገራት፤ ኢድ አል-ፈጥርና ኢድ አል-አድሃ ሕዝባዊ በዓላት ናቸው።  

የጋራ ፀሎቶች በአካባቢ ቤተ መስጊዶችና የማኅበረሰብ ማዕከላት ይካሔዳሉ፤ ሰዎችም አንዳቸው አንዳቸውን ' የተባረከ ኢድ' በሚል 'ኢድ ሙባረክ' ይባባላሉ።   

ቤተሰቦችና ወዳጆች አንዳቸው አንዳቸውን ይጎበኛሉ፤ እንዲሁም በኢድ ወቅት የማኅበረሰብ መሰባሰቦች የተለመዱ ናቸው።

"በአብዛኛው አንዱ ሌላውን የሚጠይቅበት የቤተሰብ ስብስብ ክብረ በዓል ነው፤ እንዲሁም፤ በሶስቱ ቀናት የኢድ አል-ፈጥር ክብረ በዓል ግብዣዎች በምግብ፣ ልዩ ኬኮችና ገበታዎች ይደሰታሉ" ሲሉ ፕሮፌሰር ላቺር ይናገራሉ።

ይሁንና ሙስሊም አውስትራሊያውያን ከተለያዩ አገራት ልዩ ባህላዊ ልማዶቻችውን ይዘው የመጡ በመሆኑ አከባበሮቻቸው ይለያይሉ።

አሊ አዋን አውስትራሊያዊ ፓኪስታናዊ ሲሆኑ፤ በተለይ በየዓመቱ ኢድ አል-ፈጥር በመጣ ቁጥር በእጅጉ ሥራ ይበዛባቸዋል። አውስትራሊያ ውስጥ ትላልቅ ከሆኑ መድብለባሕል ኢድ ፌስቲቫሎች የአንዱ አዘጋጅ ናቸው።

የተለያዩ አመጣጥ ባላቸው ሙስሊሞች መካከል "ግዙፍ" የሆኑ ባሕላዊ ልዩነቶች እንዳሉ ይናገራሉ። እንደ የአውስትራሊያ መድብለባሕል ኢድ ፌስቲቫል ሊቀመንበርነታቸውም ሁሉንም ወደ አንድ ማሰባሰብ የእሳቸውሥራ ነው።

“የተወሰኑ ሰዎች በኢድ ዕለት የተለየ ምግብን ያበስላሉ፤ ለየት ያሉ ልብሶችንም ይለብሳሉ። የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች፣ የመድረክ ክንውኖች፣ የተወሰኑ የማፈላልጊያ መንገዶችን የመሰሉ ነገሮች ሁሉ ይኖራሉ” ሲሉ አቶ አዋን ያስረዳል።
በኢድ ፌስቲቫል ወቅት፤ የተለያዩ ክንዋኔዎችን፣ የተለዩ ባሕሎችን አንድ ቦታ ላይ በጋራ ለማምጣት እንጥራለን፤ የአውስትራሊያ ውበት ያ ነው።
አሊ አዋን፤ የአውስትራሊያ መድብለባሕል ኢድ ፌስቲቫል ሊቀመንበር
በእዚህ የሚስማሙት ፕሮፌሰር ላቺር፤ አውስትራሊያ ውስጥ የኢድ አከባበር ከማናቸውም የእስልምና እምነት ተከታይ አገራት በጣሙን ዝንቅና ብርቱ መሆናቸውን ይናገራሉ።

“አውስትራሊያ ውስጥ የሙስሊም ማኅበረሰብ ቁንጅና ምንድነው አብዛኛዎቹ አከባበሮች የሚካሔዱት ሁሉንም የተለያዩ አመጣጦች ያሏቸውን ማኅበረሰባት አንድ ላይ በጋራ ለማሰባሰብ በሚጣርባቸው የማኅበረሰብ ማዕከላትና በአካባቢ መስጊዶች ነው” ሲሉም ያስረዳሉ።.

Share