ቃለ ምልልስ- ደራሲና ገጣሚ ሰናይት ብርሃኑ
Senait Berhanu Source: Senait Berhanu
የሰናይት የበኩር ሰራ የሆነው " ነገ መቼ ነው "የግጥም መድበል ሜልበርን አውስትራሊያ የታተመ ሲሆን በመውጪው እሁድ ዲሴምበር 8 /2019 በቪክቶርያ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ማህበር ጽ/ቤት በይፋ ይመረቃል። ሰናይት የግል ህይወት ታሪኳን በተለይ ደግሞ ዝዋይ በሚገኘው የህጻናት አምባ ይኖሩ የነበሩ ህጻናት ከተበተኑ በኋላ ያስከተለው መፈናቀል ለጎዳና ህይወት የዳረጋት አጋጣሚን አንስታ አውግታናልች። ትውስታው አስከፊ ቢሆነም በሴትነቷ የደረሰባትንም የመደፈር ጉዳት ከግጥም ስራዎቿ ጋር አጣምራ ነግራናለች።
Share