“መኢሶንና ኢሕአፓ ቢተባበሩ ኖሮ ደርግ ሥልጣን አይዝም፤ የሲቪል መንግሥት ይመሠረት ነበር ብዬ አምናለሁ” ፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ
Prof Bereket Habteselassie Source: Courtesy of PD
ኢመረተስ ፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ - የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐቃቤ ሕግና የቀድሞው የኤርትራ ሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ሊቀመንበር፤ በቅርቡ ለሕትመት ስላበቁት አዲሱ ታሪክ ቀመስ ልብወለድ መጽሐፋቸው “DEFIANCE IN THE TIME OF CHAOS AND EXISTENTIAL THREAT” ይናገራሉ። የመጽሐፉ ጭብጥ በቀድሞው የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) መሪ ዶ/ር ኃይሌ ፊዳና ቤተሰብ፣ ፖለቲካ፣ ፍትሕ፣ እኩልነት፣ የሞራል ንቅዘት፣ ስደትና የፍቅር ሁለት ገጽታዎች ዙሪያ ያጠነጥናል።
Share