"ዲሞክራሲ አለ ማለት ዘረኝነት የለም ማለት አይደለም፤ ዲሞክራሲ የፖለቲካ ሥርዓት ነው፤ ዘረኝነት ከባሕል፣ ታሪክና እምነት ጋር የሚያያዝ ነው" ዶ/ር ዮናታን ድንቁ

Dinku.png

Dr Yonatan Dinku. Credit: Y.Dinku

መስከረም 3, 2016 / ኦክቶበር 14, 2023 በመላ አውስትራሊያ የተካሔደው የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ሕዝበ ውሳኔ በአብላጫ አውስትራሊያውያን የድጋፍ ድምፅ በመነፈጉ ውድቅ ሆኗል። በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ዮናታን ድንቁ የሕዝበ ውሳኔውን ሂደትና የብሔራዊ ዕርቅ መንገዶችን አስመልክተው ይናገራሉ።


አንኳሮች
  • ሕዝበ ውሳኔና ዘረኛነት
  • የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ የሕዝበ ውሳኔ ተሳትፎና ትምህርት ቀሰማ
  • ብሔራዊ ዕርቅ

Share