አንኳሮች
- የቆሰለ ወይም የታመመ የዱር እንሰሳ ከገጠመዎት በአካባቢዎ ወደሚገኝ የዱር እንሰሳት ትድግና አገልግሎት በመደወል የባለ ሙያ እርዳታ ይጠይቁ
- ለቆሰለ ወይም ለታመመ የዱር እንሰሳ እርዳታ በሚያደርጉበት ወቅት የእርስዎም ሆነ የእንሰሳው ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጡ
- የእንሰሳት ሐኪም ለቆሰለ ወይም ለታመመ የዱር እንሰሳ መርመራ ያካሂዳል፤ እንዲሁም ለዱር እንሰሳት ቀጣይ ክብካቤና ማገገም እገዛ ለሚያደርጉ የዱር እንሰሳት ተከባካቢዎች ጭምር እገዛን ያደርጋል
አውስትራሊያ ካንጋሩዎች፣ ዋላቢዎች፣ ዎምባቶች፣ ፖሰሞች፣ እንቁራሪቶች፣ ወፎች፣ እባቦችና የባሕር እንሰሳቶችን ጨምሮ የተወሰኑ በዓለም በእጅጉ ዝንቅና አስደናቂ የዱር እንሰሳት መኖሪያ ናት።
እንደሚኖሩበት የአውስትራሊያ ክፍል የተለያዩ የዱር እንሰሳትን ይመለከታሉ። አለመታደል ሆኖ፤ የዱር እንሰሳት አንዳንዴ ይታመማሉ ወይም በተሽከርካሪዎች፣ መሠረተ ልማት ወይም እንደ እሳትና ጎርፍ በመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ይቆስላሉ።
የቆሰሉ ወይም የታመሙ የዱር እንሰሳት ከገጠምዎ እንደምን ደህንነትዎ በተጠበቀ ሁኔታ እርዳታ ሊያደርጉ እንደሚችሉና ለዱር እንሰሳቱ የተሻለ የሕክምና ዕድልን ለመቸር፣ እንዲያገግሙና ሲልም ወደ ዱር ተመልሰው እንዲሄዱ ለማስቻል የባለሙያ እገዛን ከየት ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ በጣሙን ጠቃሚ ነው።
Wael laef veterinarian Dr Tania Bishop - WIRES.jpg
ውስጥ በመኪና እየተዘዋወሩ ሳለ፤ በተለይም በገጠር አካባቢዎችና ጀምበር ስትጠልቅና ስትፈነጥቅ የዱር እንሰሳት ሲጓዙ መኪና ውስጥ ሆኖ መመልከት እንግዳ ነገር አይደለም።ታንያ ቢሾፕ
ዶ/ር ቢሾፕ "ካምፕ ሠፍረው ወይም ለጉብኝት ወጥተው ያሉ ከሆነ ከዱር እንሰሳት ጋር የመገጣጠም ከፍ ያለ ዕድል አለ፤ ኮሽታ ባላሰሙ ቁጥርም ይበልጡን የመመልከት ዕድል ይኖርዎታል” ይላሉ።
Stradbroke Island in Queensland, Australia Source: iStockphoto / Kevin LEBRE/Getty Images/iStockphoto
የቆሰሉ ወይም የታመሙ እንሰሳትን ሲመለከቱ፤ የባለ ሙያ እርዳታን ይጠይቁ።
በተለይም እንደ ካንጋሩዎች፣ ዎምባቶችና ወይም ኮኣላ የመሳሰሉ ከፍ ያሉ የቆሰሉ ወይም የታመሙ የዱር እንሰሳትን ማግኘቱ አዋኪ ሊሆን ስለሚችል፤ ዶ/ር ቢሾፕ በተቻለ ፍጥነት የባለ ሙያ እርዳታን መጠየቅ እንደሚገባ ምክረ ሃሳባቸውን ሲለግሱ፤
“ይህም ከአካባቢው የእንሰሳት ሐኪም ወይም የማዘጋጃ ቤት ጠባቂ አንስቶ እስከ የዱር እንሰሳ ክብካቤ የስልክ መስመር ወይም የዱር እንሰሳትን ታድገው የሚያሻቸውን ክብካቤ ከሚቸሩ የዱር እንሰሳት ታዳጊ ድርጅት ጋር የሚያገናኝዎት የሞባይል ስልክ ኧፖች ድረስ ይደርሳል። አውስትራሊያ ውስጥ በእያንዳንዱ ክፍለ አገርና ግዛት ውስጥ የዱር እንሰሳት ትድግና እና ክብካቤ ድርጅቶች አሉ። እናም የዱር እንሰሳት ክብካቤ ድርጅቶቹን የስልክ መስመር የት እንደሚገኙ በኦንላይን መፈለግ ይችላሉ” ይላሉ።
እንዲሁም የእራስዎንና የሌሎችንም ደህንነት ስለ ማስቀደም ጠቃሜታ ሲናገሩ፤
“በተለይም የዱር እንሰሳትን ከመንገድ ወጣ ብለው ካገኙ፤ የእራስዎን ደህንነት ጨምረው፤ ሁሌም መኪናዎን ደህንነት ያለበትና በግልፅ የሚታይበት ማቆሚያ ፈልገው ማቆምዎን እርግጠኛ ይሁኑ። የቆሰለ የዱር እንሰሳ በፍራቻ የተመላ ሊሆን እንደሚችልና ቆስሎ ሳለም ራሱን ለመከላከል እንደሚጥር ልብ ይበሉ” ሲሉ ዶ/ር ቢሾፕ ያሳስባሉ።
A bettong with a cast and bandage on its fractured leg - WIRES.jpg
የጭንቀት መጠንን ለመቀነስ በተቻለ መጠን ማናቸውንም የዱር እንሰሳት በፀጥታና በእርጋታ መቅረብ ጠቃሚ ነው። ደህንነትዎን በጠበቀ መልኩ መከወን የሚችሉ ከሆነ በተቻለ መጠን ለእንሰሳቱ ሙቀትና ጭንቀትን የሚቀንስ፤ ግና እንዲተነፍሱ የሚያስችል ፎጣ ወይም የቅርጫት ልብሶችን በማልበስ በአስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ ያድርጉ።ታንያ ቢሾፕ
ልክ እንደ ካንጋሩዎች፣ ዋላቢዎችና ፖሰሞች ልጇን በዕቅፍ የምትይዝ የሞተች አጥቢ ማርሱፕያል ከገጠምዎ፤ ምናልባትም ታቃፊ ልጅ የእንሰሳይቱን ማቀፊያ አካል ውስጥ መኖር አለመኖርን ማጣራት ጠቃሚ እንደሆነ ዶ/ር ቢሾፕ ሲያስገነዝቡ፤
“ልጁ ፀጉራማ ቆዳ ያለው ከሆነ ብቻ ያውጡ፤ ይሁንና ፀጉራማ ቆዳ የሌለው ከሆነ ግና በእዚያ ዕድሜ ጥርሱ ከእናቱ ጡት ጋር የተያያዘ ስለሚሆን ብርቱ ጉዳት ላለማድረስ ሊከወን የሚገባው በባለሙያ ይሆናል። ትንሹ እንሰሳ ሞቅ ያለና ጨለማማ አካባቢ ሊቀመጥ ይገባል። በተቻለ ፍጥነትም እናቱን ሲያጣ የመንፈስ ሁከት ስለሚገጥመውና በቀላሉም ለሞት ስለሚዳረግ የባለሙያ ክብካቤን እንዲያገኝ ማድረግ ይገባል” ብለዋል።
መኪናዎ ውስጥ መደበኛ የዱር እንሰሳት የመጀመሪያ ሕክምና መስጫ ይያዙ
ዶ/ር ቢሾፕ የተወሰኑ በቀላሉ ከቤት ውስጥ የሚገኙ ለዱር እንሰሳት የመጀመሪያ ሕክምና መስጫ የሚሆኑ ቁሶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ሲናገሩ፤
“ማለፊያ ለመዳፎች ማሰሪያ የሚሆን የተወሰነ የዱር እንሰሳት የመጀመሪያ ሕክምና መስጫ ቀዳዳ የሌለው ክሮቹ ያልተረተሩ ወፍራም ፎጣን አካትቶ፤ የካርቶን ሳጥን ወይም የእንሰሳት ማጓጓዣ፣ ወፍራም የጓሮ አትክልት የእጅ ጓንቶች፤ ከተቻለም፤ ለእናት አልባው ሕፃን እንሰሳ ማስተኛ የሚሆን ትራስ” በማለት ያመላክታሉ።
የቆሰሉ የዱር እንሰሳት በተቻለ ፍጥነት በእንሰሳት ሐኪም ሊመረመሩ ይገባል። ለእንሰሳቱ የሚያስፈልጓቸው ነገሮች ውስብስብ ስለሆኑ የአውስትራሊያ የዱር እንሰሳት በሕግ ክብካቤ ሊደረግላቸው የሚገባው የግድ ስልጠናና ፈቃድ ባላቸው የዱር እንሰሳት ተከባካቢዎች ነው።
A young wallaby under general anaesthetic in a wildlife hospital receiving treatment for a fractured leg - WIRES.jpg
ሞርጋን ፊልፖት የዱር እንሰሳት ተከባካቢ ሲሆኑ፤ የቆሰሉና የታመሙ እንሰሳትን በመከባከብ ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ አሳልፈዋል።
“እኛ እንደ ተከባካቢ ከታዳጊዎች በስልኮቻችን ላይ የማሳሰቢያ መልዕክቶች ይደርሱናል። ከዚያም በጥቅሉ ከማኅበረሰብ አባላት ጋር ግንኙነት በማድረግ ዝርዝር መረጃዎችን ከተቀበልን በኋላ ቀሪው የእኛ ፈንታ ይሆናል። እንደ እውነቱ ከሆነ እንሰሳቱ በጣም በአስቸኳይ የእንሰሳ ሐኪም ዘንድ ደርሰው ምርመራ ሊደርግላቸው ይገባል” ሲሉ ያስረዳሉ።