መምህርና ሃያሲ ዘሪሁን ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ መምህርነት እና አማካሪነት እያገለገሉ እንደነበር የሙያ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ በ48 ክፍል በቴሌቪዥን ድራማ ለሚቀርበው "ፍቅር እስከ መቃብር" ሙያዊ ሀሳባቸውን ማካፈላቸው ይታወቃል።
የአንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በ9፡00 ሰዓት በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይፈጸማል፡፡