ወደ አውስትራሊያ መጤ ለሆኑ አረጋውያን ማኅበራዊ ገለልተኝነትና የቋንቋ ችግር፣ ለጉስቁልና በሚዳረጉበት ወቅት አቤቱታ ለማቅረብ እንዳይችሉ ተጨማሪ መሰናክሎች ይሆኑባቸዋል። ይሁንና መጤ ማኅበረሰባትን ለመርዳት የሚያስችሉ እገዛዎች አሉ።
አረጋውያንን ለጉስቁልና መዳረግ ምንድነው?
የዓለም የጤና ድርጀት አረጋውያንን በአንድ ወቅት ወይም በተደጋጋሚ ሆን ብሎ ማጎሳቆል፣ ወይም "በእምነት ማጉደል ሳቢያ ለጉዳት ሲዳረጉ፣ አለያም አንድ አረጋዊ ግለሰብ ለጭንቀት ሲጋለጥ" ተገቢ እርምጃን አለመወሰድ አረጋውያንን ለጉስቁልና እንደመዳረግ ይፈርጀዋል።
አረጋውያንን ማጎሳቆል ከዓለም ሕዝብ 10 ፐርሰንቱን ቢያካትትም ብዙውን ጊዜ ግና በሪፖርትነት አይቀርብም።
90 ፐርሰንት ያህሉ አረጋውያንን ለጉስቁልና የመዳረግ ሁነቶች ተከስተው ያሉት በቤተሰብ አባላት ነው። የAdvocare ዋና ሥራ አስፈጻሚ ግሬግ ማህኒ “የAdvocare ተሞክሮዎችና ጥናታዊ ምርምሮች የሚያሳዩት በአብዛኛው አረጋውያንን ለጉስቁልና ዳራጊዎች ሴቶችና ወንዶች ልጆች መሆናቸውን ነው የሚያመለክቱት” ብለዋል።
ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ወይም የትምህርት ደረጃ ያላቸው አረጋውያን በአብዛኛው በቤተሰባቸው ወይም በጓደኞቻቸው ለመጎሳቆል የተጋለጡ ናቸው።
ምልክቶቹ ምንድናቸው?
ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ወይም የትምህርት ደረጃ ያላቸው አረጋውያን በአብዛኛው በቤተሰባቸው ወይም በጓደኞቻቸው ለመጎሳቆል የተጋለጡ ናቸው።
አንዳንዴ በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጉስቁልናዎችን በውል ለመለየት ያውካል። የተካሄደባቸው የጉስቁልና ተግባር ምናልባትም የረቀቀ ይሆናል፤ አሊያም አረጋውያኑ ስለ ጉዳዩ መናገር አይሹም። ለምሳሌ ያህል፣ ከአንድና ሁለት የቤተሰብ አባላት ባሻገር የማኅበረሰብ ድጋፍ የሌላቸውን አረጋውያን ለመጠቀሚያነት የሚገለገሉባቸውም ሰዎች አሉ።
“እንዲህ ላሉ ሰዎች አረጋውያን ስለምን እንደሚፈርሙ በማያውቁት ጉዳይ ላይ እንዲፈርሙ ማስደረግ በጣሙን ቀላል ነው።” የአረጋውያን መጦሪያ፤ ሥራ አስኪያጅ አሌግዛንደር አብራሞፍ
አንዱ የተዘወተረ አረጋውያን ጉስቁልናን የማድረሻ መንገድ ንዋይ ነው
አረጋውያንን ለጉስቁልና መዳረግ በአካል ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ ሥነ ልቦናዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ማግለልንም ያካትታል።
ይበልጡኑ ተዘውትሮ የሚከሰተው ግና ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ነው። ከአረጋውያን ገንዘብን በመስረቅ፣ የውርስ ሰነዶችን እንዲለውጡ ማስገደድ ወይም የባንክ ዶክሜንት ላይ ፊርማቸውን አስመስሎ መፈረምን ያካትታል።
የተወሰኑ ሰዎች የነገረ ፈጅ ሥልጣንን በመጠቀም የገንዘብና ሕጋዊ ጉዳዮቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር አረጋውያንን ለጉስቁልና ይዳርጋሉ።
“የቋንቋ ችሎታ ውስንነት የመጤዎችን ብይነመረብ ያጠብባል፤ እንዲሁም በፋይናንስና ሕጋዊ ውሳኔዎቻቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል።” - የአረጋውያን መጦሪያ፤ ሥራ አስኪያጅ አሌግዛንደር አብራሞፍ
እገዛን እንደምን ያገኛሉ?
በየትኛውም የአውስትራሊያ ክፍለ ሃገራትና ክፍለ ግዛታት ውስጥ በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጉስቁልናዎች አስመልክቶ ሪፖርት ማድረግን ግድ የሚያሰኙ ድንጋጌዎች የሉም።
ይሁንና፤ እያንዳንዳቸው ክፍለ ሃገራትና ክፍለ ግዛታት ለጉስቁልና የተዳረጉ አረጋውያንን የሚያግዝ ተቋማት አላቸው። በራስዎ ላይ ደርሶ ከሆነና እንዲሁም ሌላ ለጉስቁልና የተዳረጉ አረጋውያንን የሚያውቁ ከሆነ ሁሌም ለችግሮቹ አሥፈላጊውን እርዳታ የሚቸሩ አሉ።
በመጎብኘት በሚኖሩበት ክልል እርዳታ ሰጪ ተቋማትን ይፈልጉ።
ራስዎ ወይም ሌሎች አረጋውያን ለጉስቁልና ከተዳረጉ አሥፈላጊውን እርዳታን የሚሰጥ አለ።
ሆኖም ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች እንግሊዝኛ ቋንቋን በውል የማይናገሩ ከሆነ ችግርን ሪፖርት ማድርግ አዋኪ ይሆናል። ከእንግሊዝኛ ሌላ ቋንቋን የሚናገሩ ከሆነ ብሔራዊ የትርጉምና ትርጁማን አገልግሎትን (TIS) በ 13 14 50 ደውለው ያነጋግሩ። ራስዎ ደውለው መነጋገር የማይችሉ ከሆነ ግና ሐኪምዎን፣ የሃይማኖት መሪዎን ወይም እምነት የሚጥሉበትን ወዳጅዎን ደውለው እንዲያነጋግሩልዎት ማድረግ ይችላሉ።
ግንዛቤን ማስጨበጥ
የተባበሩት መንግሥታት ራስን መቻል፣ ተሳትፎ፣ ክብካቤ፣ ራስን ለስኬት ማብቃትንና ለአረጋውያን ክብር የማጎናጸፍን መርሆዎች ይደግፋል።
በአብዛኛው አረጋውያን በራሳቸው ቤተሰብ አባላት ለጉስቁልና እንዳይዳረጉ ጁን 15 ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ጉስቁልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን እንዲሆን ይሁንታን የቸረው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ነው።
የዚህ ዓመት ግንዛቤ ማስጨበጫ ቃል ‘የአረጋውያን ጉስቁልናን ማስቆም እንችላለን’ የሚል ነው። በማኅበረሰብ ዝግጅት ወይም በራስዎ ዝግጅቶችን በማስተናገድ መሳተፍ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በዕለቱ ሐምራዊ ልብስ በመልበስ፣ ዛፍ በመትከል፣ የጠዋት ሻይ በማዘጋጀት፣ አለያም የእግር ጉዞ በማሰናዳት ግንዛቤን ማስጨበጥ ይችላሉ።
በይበልጥ ለመረዳት፤
በቋንቋዎ መረጃን ያፈላልጉ:
ጠቃሚ ሊንኮችና ስልክ ቁጥሮች
Helpline: 1300 368 821
Helpline: 1800 628 221
Helpline: 1300 724 679 (Perth)
1800 655 566 (rural)
Helpline: 02 6205 3535
Helpline: 131 444
Helpline: 1300 651 192
Helpline: 08 8232 5377 (Adelaide)
1800 700 600 (rural)
Helpline: 1800 441 169