አንኳሮች
- የወንዶች የባሕሪይ ለውጥ ፕሮግራሞች የቤት ውስጥ አመፅ ግንኙነቶች ላይ የነበሩ ወንዶችን ወደ አዎንታዊ ለውጥ ለማሸጋገር ያግዛሉ
- የመድብለ ባሕል ማኅበረሰባትን ለማካተት የተመጠኑ ባሕላዊና ቋንቋዊ ፕሮግራሞች እየፈለቁ ነው
- የቤተሰብ ግንኙነቶችን ለማሻሻል አንዱ ቁልፍ ነገር ከአውስትራሊያ አኗኗር አኳያ የቤት ውስጥ ኃላፊነቶች ለውጥን መቀበል አንዳንዴ አስፈላጊ ነው
አውስትራሊያ ውስጥ መልካም ሕይወትን የመገንባት ሕልም ወደ አገሪቱ የዘለቁ በርካታ አዲስ መጤዎች የጋራ ሕልም ነው።
ይሁንና ሕልሙ ሳንካዎች ሊገጥሙት ወይም በግንኙነቶች ፍፃሜ ሊያበቃ ይችላል።
የግብረ የቤት ውስጥ የቤተሰብና ወሲባዊ አመፅ ሥራ አስኪያጅ ጄሲካ ሃርኪንስ አሠአ ከ ጋር በሽርካነት ዕድሜያቸው ከ18 በላይ ለሆነና በቤት ውስጥ ግንኙነታቸው አመፅን ይጠቀሙ ወይም ጎንታይ ባሕሪይ ለነበራቸው ወንዶች ፕሮግራም እንደሚካሂድ ተናግረዋል።
አውስትራሊያ ውስጥ ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ እየተካሔደ እንደሁ አስረድተዋል። ማንም ተዘንግቶ እንዳይቀር፤ ወንዶች በአዲስ አገር ለውጦችን እንዲቃኙ ለማገዝ የሚያስችሉ በልክ የተመጠኑ ባሕላዊ ፕሮግራሞች ተጀምረዋል።
ወ/ሮ ሃርኪንስ "በአብዛኛው ፕሮግራሞች ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ መደብ ጀርባ ያላቸውን አያቅፉም ወይም ፍላጎቶቻቸውን አይረዱም" ብለዋል።
Feelings of unmet dreams don't need to end up in violence.
ሃርኪንስ ማኅበረሰባቱ የተመረጡት SSI በሌላ አካባቢዎች ከእነሱ ጋር አብሮ እየሠራ በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። አክለውም፤ ማንኛውም ሕብረተሰብ ከሌላው ሕብረተሰብ የተለየ የአመፅ መጠኖች ስለመኖራቸው የሚያሳይ ማስረጃ የለምም ብለዋል።
የሊባኖስ ተወላጅና የቀድሞው የጠንካራ ቤተሰቦች ግንባታ ፕሮግራም አስተባባሪ ጋሳን ኑጃኤይም፤ በተወሰኑ ባሕሎች ወንዶች በአብዛኛው የቤተሰብ ራስ ተደርገው ይወሰዳሉ ብለዋል። በማያያዝም የቤት ራስ ከሆነው ወንድ የቤት ወጪ ሸፋኝነት ይጠበቃል፤ እንዲሁም እሱን ማድመጥና መከተልንም ግድ እንደሚል ተናግረዋል።
አቶ ኑጃኤይም፤ በአብዛኛው ቀደም ሲል በክህሎት የተመላ ባለሙያ የነበረው በሠፈራ ሳቢያ አውስትራሊያ ውስጥ በተለያዩ አስባቦች ሥራ አጥ በመሆን ዕልባት ያልተበጀለት ስሜታዊ ጭንቀት መኖሩን አስረድተዋል። .
ካለቀስኩ፤ ወንድ አይደለሁም። እርዳታ ከጠየቅኩ ወይም ደካማ ከሆንኩ፤ ወንድ አይደለሁም።ጋሳን ኑጃኤይም
ወንዶች በአብዛኛው ውስብስብ በሆኑ ባሕላዊ ዕሴቶች፣ እምነቶች፣ ልማዶች፣ ተጠባቂነትና የወንድነት ዕሳቤዎች ተጠምደው እንዳሉ እንደሚሰማቸው አክለዋል።
ይሁንና ዕውን ያልሆኑ ሕልሞች ስሜት በአመፅ ሊጠናቀቁ አይገባቸውም።
ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ የሕይወት አሰልጣኝና የግንኙነቶች ምክር አገልግሎት ቡድን መሪ እንደሆኑት ዶ/ር ሳምቦ ንዲ አባባል፤ ጥሩ ሕይወትን ለመኖር ያሉ ጥቂት ተግዳሮቶችን መገንዘብና ማመልከት በአንድ በኩል ተገዳዳሪና ፈታኝ ቢሆንም፤ አዎንታዊ ለውጦችን ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።
ዶ/ር ንዲ፤ ከሰዎች የቀድሞ ማንነቶች ጋር የተያያዘ ሚና አንዳንዴ በአዲስ ሥፍራ ለድንገተኛ ባዶነት እንደሚዳርግ ይናገራሉ።
ሴት የቤት ወጪ ሸፋኝ ስትሆንና በተቃራኒው ወንድ የቤተሰብ ተከባካቢ ሲሆን፤ ልማዳዊ የፆታ ሚናዎችን ማጣት በአብዛኛው ቤተሰቦች ውስጥ ዕውን ይሆናል።
እውነታው የሚና መለዋወጥ ጠቀሜታዎን ያነሰ ወይም ከተለየ ሁኔታ አኳያ የአኗኗር ለውጥን አስፈላጊ እውነታን መቀበል አስተዋፅዖዎን ዝቅ ያለ አያደርገውም።ዶ/ር ሳምቦ ንዲ
አደላይድ ውስጥ አፍሪካውያን ወንዶችን፣ ሴቶችንና ወጣቶችን ስለ ቤተሰብና የቤት ውስጥ ጥቃት ለማስተማር የ ን ይመራል።
ዶ/ር ንዲ የቤተሰብ ጥቃት በአብዛኛው አይነኬ ርዕስ ሆኖ የሚታይ በመሆኑ፤ ብርቱ ለውጦች ዕውን የሚሆኑት ሰዎች በግልፅ አስተማማኝና ድጋፍ ባለበት አካባቢያዊ ሁኔታ እንደሁ ይናገራሉ።
"አንድን ሰው የመምታት አካላዊ ገፅታን፤ እንዲሁም በስሜታዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ ወሲባዊ ወይም ሌላው ቀርቶ የገንዘብ በደልን የመፈፀም ዙሪያ መነጋገር መቻል ሳይቀር ይረዳሉ" ሲሉም።
ዶ/ር ንዲ የማኅበረሰብ አባላት የአውስራሊያ ሕይወታቸውን እያዳበሩ ሳለ፤ ማለፊያ ሕይወትንና ጠንካራ ቤተሰብን መገንባት ምን ማለት እንደሁ፤ አንዳቸው የአንዳቸውን አመለካክቶችና ተሞክሮዎች በመቃኘት እንዲማማሩ ያበረታታሉ።
እናም አንዳንዴ፤ የፆታ ሚናዎች ለውጥ አንዱ ከአንዱ ጋር በተለየ ሁኔታ መገናኘት ሊሆንም ይችላል።
Men's mental health matter, because their mental health and overall well-being are fundamental to the overall wellbeing of the community.
ሽግግርዎን ከወደ ኋላዎ ለልጆችዎ የሚተዉትን ውርሰ አሻራ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይጀምሩ ሲሉ አተያያቸውን ይቸራሉ።
አቶ ኪንግ "ስለ እርስዎ ምን እንዲሉ ይሻሉ? አመሰግናለሁ አባቴ፤ ስለ እውነት አደንቃለሁ አንተ…የመቋጫ ዐርፍተ ነገራቸው ምን ይሆን?" ይላሉ።
እንደ አቶ ኪንግ አባባል፤ ወንዶች በአብዛኛው በአስተዳደጋቸው ወቅት አግባብ ባልሆነ መልኩ ወንድነት የተሳለበትን የውስጣዊ ስሜት መግለጫዎች ይማራሉ።
አለመታደል ሆኖ፤ ወንዶች እያደጉ ሲሄዱ ስሜቶቻቸውን ከግንኙነታቸው መደበቅን ይማራሉም ይላሉ።
አቶ ኪንግ አሮጌ አስተሳሰቦችን መተውና የኔ ለሚሏቸው ስሜትዎን ያሳዩ ወይም ቀውስ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ሙያዊ እርዳታን ይጠይቁ ሲሉ ያበረታታሉ።
ታምቀው የተያዙ ውጪያዊና ውስጣዊ ስሜቶች አንዳንዴ እንደ እሳት ገሞራ ሊፈነዱ፣ ወደ አዋኪ ባሕሪያትም ሊያመሩ እንደሚችሉም ይናገራሉ።
ምክረ ሃሳቦቻቸውም ወሳኝ ከሆነ ውሳኔ በፊት የሚከተሉትን የተግባቦት ብልሃቶች ማዳበርን ያካትታሉ፤
- የሌላውን ሰው አተያዮች ለመስማት ዝግ ይበሉ
- ለእርስዎ አመለካከቶች እንደሚገዙ ሳይጠብቁ የሌላውን ሰው ዕሳቤዎች ያክብሩ
- ለዕሳቤዎችዎና ስሜቶችዎ ዕውቅናን ይችሩ
- ኃይልዎ ማዕከል እንዲሆን አረፍ ይበሉ
- ወሳኝ ከሆነ ውሳኔ ላይ ከመድረስዎ በፊት ዘና ይበሉ
- ከውሳኔዎ በፊት እንደ አልኮል ያሉ አስካሪ ነገሮችን አይጠቀሙ
Men are often fathers, brothers, and partners, and their mental health has a direct impact on their families. A man's wellbeing can influence the emotional health of his loved ones.
አንዳንዴ መታገል ምንም አይደል። አውጥቶ መናገር ምንም አይደል፤ እንዲሁም እርዳታን መጠየቅም ምንም አይደል።ዶ/ር ሳምቦ ንዲ
ተመሳሳይ የሆኑ ፕሮግራሞችን በመላ አገሪቱ ከግንኙነቶች አውስትራሊያ ማግኘት ይችላሉ ወይም በአካባቢ የስልክ ጥሪ ዋጋ 1300 364 277 መደወል ይችላሉ።
የውስጣዊ ስሜት ወይም የግንኙነት ስጋቶች ያሉባቸው ወንዶች ወደ አውስትራሊያ ለነፃ የምክር አገልግሎት ድጋፍ በቀን 24 ሰዓት አገልግሎት በሚሰጠው 1300 78 99 78 መደወል ይችላሉ።