የአድዋ ድል በአዲስ አበባ ነዋሪዎች አንደበት
ሌሎች አገራት የሚያከብሩት ከቅኝ ግዛት ነፃ የወጡበትን ቀን ነው፤ እና የምናከብረው የአድዋ በዓል የድል ቀን ነው።
አድዋ ለእኔ አገር ነው፤ ባለ አገር መሆን ማለት ነው።
የአድዋን ድል በየዓመቱ ሳይሆን በየቀኑ ነው የማስበው። ለእዚህች ዋጋ የተከፈለላት አገር ምን አደርጋለሁ ብዬ በየቀኑ ራሴን እጠይቃለሁ። እንደዚያ ነው የአድዋ ድልን የማከብረው።
የአድዋን በዓል በጣም ልጅ ሆኜ አክብሬያለሁ። ጊዮርጊስ አጥር ላይ ተንጠልጥዬ ጀግኖችን አይቻለሁ።
128ኛው የአድዋ ድል እንደምን ሊከበር ይገባል?
የአድዋ ድል በዓል ሲከበር የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ቢከበር፤ እርዳታ ቢሰጥ ይጠቅማል። ጀግኖቻችን ደማቸውን ከፍለዋል፤ እኛ ገንዘባችንን ከፍለን ሕዝባችንን ልንታደግ ይገባል።
የአድዋ ድል በእኛ የልጅ ልጆቻቸው መከበር ያለበት በአንድነት ነው።
መስቀል አደባባይ ላይ ትርዒቶች ቢካሔዱ ደስ ይለኛል።
ኢትዮጵያዊነትን በማሰብ አሁን ያሉብንን የመከፋፈልና የመራራቅ ችግሮች አሸንፈን በአንድነት መጥተን ቢከበር ደስ ይለኛል። አዲሱን የአድዋ ሙዚየም ፕሮጄክት ዕውን ላደረጉት ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።