ተግዳሮትና መልካም ዕድል
ዕፀገነት አሰፋ፤ ሀገረ አሜሪካ ዘልቀው እንደ አዲስ ሠፋሪ ፍልሰተኛነታቸው በማኅበራዊና ግላዊ ተግዳሮቶች ውስጥ አልፈዋል።
አሜሪካ ከምትቸራቸው መልካም ዕድሎችም ተቋድሰዋል።
በፋርማሲ የሙያ ክህሎት ዘርፍ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ለዱክትርና በቅተዋል።
Etsegenet Assefa - Graduation. Credit: E.Assefa
ዶ/ር ዕፀገነት፤ በተለይም ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ለሚመጡ የፋርማሲ ሙያተኞች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ቅድመ ዝግጅቶችን አንስተው ይመክራሉ።
ብሔራዊ የፋርማሲ ቦርድ ፈተና በመውሰድ የሙያ ዕውቅናን ለማግኘት፤
- Test of English as a Foreign Language (TOEFL)
- Foreign Pharmacy Graduate Examination Certification (FPGEC)
ማግኘትን ግድ እንደሚላቸው ያስገነዝባሉ።
ወደ ፋርማሲ መስክ መዝለቅ የሚተልሙ ወጣቶች ቀደም ብለው ስለ ሙያው ጠለቅ ያለ ጥናት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ያሳስባሉ።
ሙያው፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየተተካና ብርቱ ፉክክሮች ያሉበት በመሆኑም ከሌሎች ልቆ መገኘትን ግድ እንደሚል ልብ ያሰኛሉ።
ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው በነበረት ወቅት የፋርማሲ ባለሙያ ያልሆኑ ግለሰቦች በፋርማሲ መስክ መሰማራታቸውን መረዳታቸው ለሕዝብ ጤና ያለውን አሳሳቢነት ያመላክታሉ።
ከዶ/ር ዕፀገነት ጋር ያካሔድነው ቃለ ምልልስ በእዚሁ አልተቋጨም፤ በቀጣዩና የመደምደሚያ ክፍለ ዝግጅታችን፤ ከፋርማሲ ሙያቸው ጎን ለጎን ስለሚያካሒዱት የቤት ሽያጭና ግዢ የንግድ መስክ አንስተው ይናገራሉ።
ተጨማሪ ያድምጡ
ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ከመሃል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ
ተጨማሪ ያድምጡ
ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ፋርማሲ - የቤት ሽያጭና ግዢ