በዓለ ትንሣኤ በአውስትራሊያ፤ ከሃይማኖት ባሻገር የማኅበራዊና ባሕላዊ ልማዶች ዳሰሳ

Australia Explained - Easter

Social and cultural Easter traditions Australians follow, beyond religion Credit: Fly View Productions/Getty Images

በዓለ ትንሣኤ ለክርስቲያኖች ትልቅ ፋይዳ አለው። ይሁንና ለሌላ እምነት ተከታዮች ወይም ከቶውንም አማኝ ላልሆኑቱም፤ የአራት ቀናት የዕረፍት ሐሴትን ይቸራል። በከፊል ለቤተሰብና ማኅበራዊ ስብስብ፣ ከቤት ውጪ እንቅስቃሴዎች ተሳትፎና ልጆች ማዕከላዊ መድረኩን ለሚይዙባቸው ኩነቶች መታደሚያነት። ፋሲካን አውስትራሊያ ውስጥ ለማክበር አሥፈላጊ መመሪያዎን እነሆን።


አንኳሮች
  • ፋሲካ አውስትራሊያ ውስጥ በመኸር ወቅት የሚውል በእንቅስቃሴ የሚከበር፤ በአብዛኛውም ከትምህርት ቤት የዕረፍት ቀናት ጋር የሚገጣጠም ነው
  • ከሃይማኖታዊ ፋይዳው ባሻገር፤ ፋሲካ በባሕላዊ ዕይታ ለቤተሰብ መሰባሰቢያ፣ የማኅበረሰብ መገናኛ፣ የጉዞ፣ ፌስቲቫሎችና የከቤት ውጪ እንቅስቃሴዎች መከወኛ ተደርጎ ይታያል
  • የፋሲካ ቢብሊ የፋሲካ ጥንቸልን የቸኮሌት ዕንቁላሎች ያዥነት እየተካ ያለ ልዩ የአውስትራሊያ ልማድ ነው
በክርስትና እምነት፤ በዓለ ትንሣኤ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ይዘክራል። የትንሣኤ ቅዱስ ሳምንት ማብቂያ የሆነው ዕለተ እሑድ በክርስትና ዘመን መቁጠሪያ በጣሙን ደምቀው ከሚከበሩት ክብረ በዓላት አንዱ ነው።

ፋሲካ ሲነሳ ለአውስትራሊያውያን በተለምዶ የአራት ቀናት ረጅም የሳምንት መጨረሻ ማለት ነው፤ ዕለተ ስቅለት፣ ዕለተ ትንሣኤና የትንሣኤ ሰኞ በተቀሩት ክፍለ አገራትና ግዛቶች የሕዝባዊ በዓል ቀናት ናቸውና።

የሊባኖስ ዝርያ ያላቸው የሲድኒ ነዋሪ የሆኑት ዳንዬሊ ኮሪ ያደጉት የኦርቶዶክስና ካቶሊክ ፋሲካን በማክበር ነው።

በርካታ ሰዎች ለጉዞ፣ ጊዜያቸውን ከቤት ውጪ ለማሳለፍ ወይም ፌስቲቫሎች ላይ ለመታደም ከሥራ ገለል እንደሚሉ ሲገልጡ፤

“የተለየ አመጣጥ ያላቸው ሰዎችም ያከብሩታል፣ የትምህርት ቤቶች ዕረፍት ጊዜያትም አሏቸው፤ እናም ያ ለቤተሰብ ተጨማሪ ጊዜን ይሰጣቸዋል ወይም ወደ ሌላ መዳረሻ ሥፍራዎች እንዲጓዙ ያስችላቸዋል። ፋሲካ አውስትራሊያ ውስጥ የሚውለው በመኸር ወቅት በመሆኑ፤ በርካታ እንደ የብረት ምጣድ መጥበሻ ጥብሶችን የመጥበስና ሽርሽሮችን ማድረግን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ” ይላሉ።
Australia Explained - Easter
Children can make their own basket as an arts & crafts activity to use for their Easter egg hunt. Credit: Fly View Productions/Getty Images

የልጆች የፋሲካ ልማዶች

በሜልበርን ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ልጅነት ትምህርት ተመራማሪ የሆኑት ሊዛ ቤከር፤ ፋሲካ ለታዳጊ ልጆች ጨዋታዎችና እንቅስቃሴዎች የሚገናኙበት ወቅት እንደሁ ሲናገሩ፤

“ለቅድመ ትምህርት ቤት ልጆች ወይም ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዕድሜ ለደረሱ ልጆች፤ ገዝፈው የሚታዩት የፋሲካ ምልክቶች የሆኑት የፋሲካ ዕንቁላሎችና የፋሲካ ጥንቸል ናቸው።

“በእርግጠኛነት፤ የቆየ ልማድ የሆነው የፋሲካ ዕንቁላል አደን አያሌ አውስትራሊያውያን ልጆች የሚደሰቱበት ነው” ብለዋል።

እንደ እሑድ ጨዋታዎች፣ የዕንቁላል ቅርፅ ያላቸው የቸኮሌት ዕንቁላሎች፣ ከረሜላዎች ወይም እውነተኛና እውነተኛ ያልሆኑ ዕንቁላሎችን ማስጌጥና የፋሲካ ዕንቁላል አደኖች በቤተሰብና በማኅበረሰብ ቡድናት በመናፈሻዎችና የጓሮ አትክልቶች ይዘጋጃሉ።

በትረካው መሠረት፤ የፋሲካ ዕንቁላሎች የሚታደሉትና የሚደበቁት በፋሲካ ጥንቸል ነው።

ይሁንና ጥንቸልን በአገር በቀል ቢልቢ በመተካት ከጥቂት ለውጥ ጋር ልማዶችን ተከትሎ የመቀጠሉ ቁጥር እያሻቀበ ነው። ጥንቸሎች በአውስትራሊያ ሥነ ምሕዳር ጎጂነት ተፈርጀው ስለሚታዩ።

“ግልፅ ነው ገና በትውውቅ ላይ ያሉ ፍጡራን ናቸው፤ በአገር በቀል እንሰሳቶቻችንና ቅጠላ ቅጠሎቻችን ላይ ሁከትን ፈጥረዋል። እናም የፋሲካ ቢልቢ ዕሳቤን ፈጥረናል”

“ልክ የፋሲካ ጥንቸሎች ቸኮሌትን እንደሚገዙ ሁሉ፤ አሁን የፋሲካ ቢልቢዎች ቸኮሌትንም መግዛት ይችላሉ” ሲሉ ወ/ሮ ቤከር ያስረዳሉ።

እንደ ብዝኅባሕል አገር፤ አውስትራሊያ ልማዶችን ባቀናጀ መልኩ ፋሲካን ታከብራለች።

ይህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በተለይም የአካታችነትና ባሕላዊ ግብረ ምላሽን ከፍ - ከፍ በሚያደርገው በብሔራዊ ሥርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ የልጅነት ትምህርት ዘርፍ አንዱ ማስረጃ እንደሁ ቤከር ያስገነዝባሉ።
መምህራንና ትምህርት ቤቶች ልጆች ስለሚያመጧቸው በርካታ ልማዶችና እነዚያንም በጋራ አዋድዶ እንዲያከብሩ ለማስቻል በጣሙን ጥንቁቅ ናቸው።
ሊዛ ቤከር
“እናም፤ ለምሳሌ የፋሲካ ቸኮሌት ዕንቁላሎች አደን ከማድረግም ባሻገር፤ እንደ ኦርቶዶክስ እምነታቸው የፋሲካ ዕንቁላሎችን በተለያዩ ቀለማት ማስጌጥን ወይም በተለየ መልኩ ዕንቁላሎችን ቀንበጦችና ቅርንጫፎች ላይ አሳምረው መስቀል ይሹ ይሆናል።
Australia Explained - Easter -  mother and child with Easter bonnet
Making an Easter hat and participating in an Easter hat parade is a classic cultural ritual, that many children and schools opt to participate in, says Ms Baker. Credit: OMG/Getty Images

ሁለት ፋሲካዎች፤ ተጨማሪ ምርጫ ለባሕላዊ ልማዶች

ከመጀመሪያና ሁለተኛ ትውልድ ሊባኖሳውያን - አውስትራሊያውያን ወላጆች የተወለደችው ወ/ት ኮሪ ያደገችው የካቶሊክና ኦርቶዶክስ ፋሲካዎችን እያከበረች ነው። .

ሁለቱ ዋነኛ የክርስትና ቤት እምነቶች ፋሲካን የሚያከብሩት በተለያዩ ቀናት ነው።

“የካቶሊክ ፋሲካ ተከታዮች የግሪጎሪያ ዘመን መቁጠሪያን ሲከተሉ፤ የኦርቶዶክስ ተከታዮች የጁሊየስ ዘመን መቁጠሪያን ይከተላሉ። አልፎ አልፎ አንድ ላይ ያክብራሉ፤ በሌላ ጊዜያት በመካከላቸው እስከ አምስት ሳምንታት ልዩነቶች ይኖራሉ" በማለት ወ/ት ኮሪ ታስረዳለች።

ሁለቱም በልማዳቸው መሠረት፤ ፋሲካ እንደ ቤተሰብ አንድ ላይ መሰባሰቢያ፣ የመስቀል ቅርፅ ያለባቸውን ዳቦች፣ ቤት ውስጥ የተጋገሩ ብስኩቶችና ኬኮችን፣ የአሣ ሾርባዎች፣ የበዓል ጥብስን አክሎ እሑድ የበዓለ ትንሣኤ ዕለት በፋሲካ ምግቦች መደሰት እንደሆነም ትናገራለች።

በኦርቶዶክስ ባሕላዊ ትግበራዎች ውስጥ አንዱ በዋነኛነት የተለመደው ዕንቁላሎችን እንደ ሽንኩርት ልጣጭ በመሰሉ ማስጌጥና ቀጥሎም የቤተሰብ አባላት እርስ በእርሳቸው ዕንቁላሎችን በመወራወር ፍልሚያ ማድረግ ነው።

ወ/ት ኮሪ ቤታቸው ውስጥ እንደምን ዕንቁላልን ይመቱ እንደነበር ሲያስታውሱ፤

“ከሌላ የቤተሰብ አባል ጋር ተቧድኖ የሚደረግ በእጅጉ በስሜት የተመላ ውድድር ነበር። የዕንቁላሉን አንድ ጎን አዙረን እንገለብጥና ሌላኛውን ጎን መታ እናደርገዋለን። እናም ዕንቁላልዎ በሁለቱም ጎኖች በኩል ከተሰበረ እርስዎ ከጨዋታው ይወጣሉ፤ በመጨረሻም ዕንቁላሉ ከየትኛውም ጎን ያልተሰበረበት ወይም ከአንድ ጎን ብቻ የተሰበረበት አሸናፊ ይሆናል” ብለዋል።
Australia Explained - Easter
Different cultural group celebrate Orthodox Easter in Australia, including followers of the Greek Orthodox, Russian Orthodox and Macedonian Orthodox faith. Credit: LOUISE BEAUMONT/Getty Images
‘የፓንኬክ ማክሰኞ’ ወይም ‘የፓንኬክ ቀን’ የሚታወቀው የፋሲካ መዳረሻ ላይ ሌላው ታዋቂ ምግብ ነክ ልማድ ነው።

“ከፋሲካ መዳረሻ ረቡዕ ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ጓዳ ውስጥ የሚከናወን ልማድ ነው” ሲሉ ወ/ት ኮሪ ይናገራሉ።

አክለውም፤ ፓንኬክ መሥራት ልጆችን የሚያሳትፍ አዝናኝ እንቅስቃሴ ነውም ይላሉ።

“በተለምዶ ቤተሰባዊ ኩነት ሲሆን፤ የዕለቱ ዕለት ሰዎች ፓንኬኮችን እንዲመገቡ የመጋበዝ ስሜትን ያሳድራል፤ ያን ማድረጉም ምንም ስህተት የለበትም" ሲሉ ይናገራሉ።”

የመገናኛ ጊዜ

በፋሲካ ወቅት ወደ ካምፕ መሔድ ወይም ፌስቲቫሎች ላይ መታደም የተለመዱ ሽርሽሮችና የአውስትራሊያውያን ተመራጭ መዝናኛዎች ናቸው።

እንደ በርካታ የሲድኒ ነዋሪዎች ሁሉ፤ ወ/ት ኮሪ በልጅነቷ የገበሬዎች ማኅበረሰባትን ኩነት በሚያክብረውና በአጭር አጠራር የፋሲካ ትዕይንት ወይም በሙሉ ስያሜው የሲድኒ ሮያል የፋሲካ ትዕይንት ላይ በመታደም ቤተሰባዊ ትዝታዎች አሏት።

“ማራኪ ተሞክሮ ነበር። እንጨት ፈለጣ ሳይቀር የገጠር፣ የአበባና የእጅ ጥበብ ሥራ ታይታዎችን ተመልክተንበታል። ለትምህርት ቤት ፕሮጄክታችን ናሙና እንጨቶችን ሁሉ ለቅመናል። እርግጥ ነው፤ የፋሲካ ትዕይንት ቦርሳዎቻችን በአስፈንዳቂ ማለፊያ ነገሮች፣ ከረሜላዎችና የድንች ጥብሶች ተሞልተውበታል” ብላለች።
Australia Explained - Easter - Princess Anne Visits Sydney
Held over a two-week period around Easter, the Sydney Royal Easter Show is Australia’s largest in size annual event, attracting over 800,000 people. Credit: Mark Metcalfe/Getty Images
በክፍለ አገሩ በዓይነቱ ግዙፍ የሆነው ፌስቲቫል ሃይማኖታዊ ትስስሮሽ የለውም፤ የፋሲካን ስያሜ የያዘው ከወቅቱ ጋር ስለሚገኛኝ ብቻ ነው።

“በፋሲካ ሰሞን ለማካሔድ ከውሳኔ ላይ የተደረሰው በ1890ዎቹ ነው፤ ምክንያቱም ረጅም የዕረፍት ጊዜ ስለሆነ ነው። ሰዎች ከንግዳቸውና ከእርሻዎቻቸው ገለል እንዲሉ አጋጣሚ ሆኗቸዋል። ለሁለት ቀናት ሳይሆን ለሶስት ቀናት። እናም እንዲያ ሆኖ በዓመቱ ውስጥ የምናከብረው የፋሲካ ትዕይንት ሆነ” ሲሉ ማሪ ዊልተን፤ የሲድኒ ሮያል ፋሲካ ትዕይንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ያስረዳሉ።

አውስትራሊያ ውስጥ ልክ እንደሌሎች አነስተኛ መጠን እንዳላቸው የፋሲካ ትዕይንቶች ሁሉ የካርኒቫል ግልቢያዎች፣ ጨዋታዎች፣ ከእርሻ እንሰሳ ጋርና የውድድር እንቅስቃሴዎች ይካሔድበታል።

አቶ ዊልተን የሲድኒ ሮያል ፋሲካ ትዕይንት ብዝኅነትን ያካትታል፤ እናም አዘጋጆች የአውስትራሊያ ዜግነት ቀንን ከዓመታዊው ስብስብ ጋር አዋድደውታል በማለት ሲያስረዱ፤

“እና አራተኛና አምስተኛ የገበሬዎች ትውልድ ከሆኑ ሰዎች ጋር ይነጋገራሉ። በ12ቱ ቀናት ውስጥ እኒህ ሁሉ ማኅበረሰባት አንድ ላይ ሆነው ማየት በጣሙን አስደሳች ነው። ስለምን ግብርናን የማስተዋወቅ የአውስትራሊያዊ ባሕል ገፅታ ናሙና ነውና" ብለዋል።
ከየትም አገር ይምጡ ያ ምንም ማለት አይደለም፤ የትኛውም ዓይነት ሃይማኖት ይኑርዎት ያ ምንም ማለት አይደለም፤ ወደ ሲድኒ ሮያል የፋሲካ ትዕይንት ሲመጡ በሮቹ ለእርስዎ ክፍት ናቸው።
ማሪ ዊልተን
እንደ ወ/ት ቤከር አባባል፤ በመጨረሻም ፋሲካ ከሌሎች ጋር ለመገናኘትና ማኅበረሰባዊ መንፈሳችንንና ደህንነት የመታደጊያ አጋጣሚ ነው።

“የአካባቢ ማኅበረሰብ ቡድኖች ወይም የትምህርት ቤት ቡድኖች ይኖራሉ፣ የአካባቢ ማዘጋጃ ቤት፣ ምናልባትም ገበያዎች ወይም ፌስቲቫሎች ወይም ኩነቶች ይኖራሉ። የአራት ቀናት ርዝመት ያለው የዕረፍት ጊዜ ነው፤ እናም ወደ ማኅበረሰብዎ ዘልቀው ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚገኙበት ነው"

“ፋሲካና ማናቸውም ክብረ በዓሎቻችን፤ ሃይማኖታዊ ወይም ማኅበራዊ ወይም ባሕላዊ ይሁኑ፤ ሰዎችን አንድ ላይ ማሰባሰብና ቤተሰባዊ ግንኙነቶችን ማድረግ ነው” ብለዋል።

Share