ሀገሬ

*** የእናት አገር ፍቅርና ርዕይ

Abay Abiy

PM Abiy Ahmed Source: Courtesy of PD and AA

እምዬ

ሀገሬ

ቀለሜ

ሕልሜ

እንኳንና በህይውት

በሞትም የማይሞት

የፈጸምነው ገድል

ያኖርነው አሻራ

ቢኖርም ዘላለም

ካባይ ግድብ ጋራ

እምዬ

ሀገሬ

ቀለሜ

ሕልሜ

ክብርሽ ከፍ ብሎ - ከሠላምሽ ጋራ

ላለም ሁሉ እንዲታይ - እንደ ንጋት ጮራ

ክንፍ ሆነው እግሮቼ - በበረርኩ ለሥራ። 


Share
Published 14 August 2020 12:13pm

Share this with family and friends