የፊፋ የዓለም ዋንጫ 2022™ ኖቬምበር 21 ቀን 2022 / ኅዳር 12 ቀን 2015 ይጀምራል። በመላ አውስትራሊያ የ SBS ቀጥታ ስርጭትም በነፃ ይተላለፋል። 64ቱም ግጥሚያዎች በሙሉ፤
- DAB ዲጂታል ራዲዮ
- ኦንላይን
- በSBS ራዲዮ ሞባይል ኧፕ ያድምጡ።
እንደምን መስማት እንደሚችሉ
ለፊፋ የዓለም ዋንጫ 2022™ ስርጭት በተመደቡ ጣቢያዎቻችን SBS Football 1, 2 እና 3 በ DAB ራድዮንዎ፣ በድረገጽ ወይም በ SBS ነፃ ራዲዮ ኧፕ እያንዳንዱ ግጥሚያ በ12 ቋንቋዎች በቀጥታ ይሰራጫል።
- SBS Football 1 (ስርጭቱን ጀምሯል)፤ በእያንዳንዱ ግጥሚያ ወቅት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማብራሪያዎች፣የዓለም ዋንጫ ዋነኛ ሙዚቃንና ሌሎችንም ወቅቶች ያክላል።
- SBS Football 2 and 3 (ኖቬምበር 14 / ኅዳር 5 ይጀምራል)፤ የእያንዳንዱን የተጋጣሚ ቡድናት ጨዋታዎች በቀጥታ በተለያዩ ቋንቋዎች ያሰራጫል።
- SBS Arabic24፤ እያንዳንዱን ግጥሚያ በአረብኛ ቋንቋ ያስተላልፋል።
ከመላው ዓለም በፊፋ የዓለም ዋንጫ™ አማካይነት ከሽርካዎች የሚቀርቡ ማብራሪያዎች በ SBS በኩል በአረብኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፖርቹጋል፣ፈረንሳይኛ፣ ጀርመን፣ ዳች፣ ክሮኤሽያ፣ ፖሊሽ፣ ጃፓንኛ፣ ኮሪያ፣ ፐርዥያና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይቀርባሉ።
ውድድሮቹ በሚካሔዱበት ወቅት SBS ራዲዮ 3 ወደ SBS እግር ኳስ 2 በመለወጥ እያንዳንዱን ግጥሚያ በተለያዩ ቋንቋዎች ያሰራጫል። በውድድሮቹ ጊዜያት የ BBC World Service ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭትን ለማድመጥ ይጎብኙ።ከቀጥታ የእግር ኳስ ስርጭት ውጪ ካለፉት የዋንጫ ውድድሮች አንስቶ ጥሩና መጥፎ የተሰኙ የብሔራዊ ቡድኖች ሙዚቃዎችን አካትቶ ያለማቋረጥ የሚተላለፉት የእግር ኳስ ገናና ሙዚቃዎች ይቀርቡበታል። የዓለም ዋንጫ ተሞክሮዎን ቀደም ብለው አሁኑኑ የ SBS Football 1 እና DAB ራዲዮ ወይም በ በማድመጥ ይጀምሩ።የእግር ኳስ ትኩሳት መዝሙሮች
- የSBS ራዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ማብራሪያዎች ሠንጠረዥ የውድድሩ መጀመሪያ ሲቃረብ ማስተካከያ የሚደረግበት ይሆናል።
የፊፋ ዓለም ዋንጫ 2022ᵀᴹ ቀናትና ሰዓታት
- የቡድን ደረጃ: ኖቬምበር 21 - ዲሴምበር 3 / ኅዳር 12 - 24
- የ16 ቡድናት የዙር ግጥሚያ: ዲሴምበር 4 - 7 / ከኅዳር 25 - 27
- ሩብ ፍፃሜ: ዲሴምበር 10 - 11 / ከታህሳስ 1 - 2
- የመጨረሻ ማጣሪያዎች: ዲሴምበር 14 - 15 / ከታህሳስ 5 - 6
- የ3ኛ እና 4ኛ የደረጃ ግጥሚያ: ዲሴምበር 18 / ታህሳስ 9
- የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ: ዲሴምበር 19 / ታህሳስ 10
.