ሰለሞን ዓለሙ በ5 ቋንቋዎች ከ500 በላይ የሬዲዮ ድራማዎችን፣ የመድረክ ቴአትሮችን እና መነባንቦችን አዘጋጅቷል።
በተለይም ከዳንኪራው ጀርባ፣ ፍራሽ ሜዳ፣ ገመዱ እና አዙሪትን የመሳሰሉ ተወዳጅ ስራዎችን እንዳበረከተ ወዳጆቹ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ሬዲዮ ታሪክ በተለይ ከ1975-1980 ገናና ስራዎችን ያበረከተበት ወርቃማ ዘመኑ ነበር።
ሰለሞን በቅርቡ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ሌሊቱን ከዚህ ዓለም ተለይቷል።