ፖድካስቶችንና የቀጥታ ራዲዮ ዜና ስርጭቶችን ለማድመጥ ወይም ከ60 በላይ ቋንቋዎችን ከSBS 1, 2 እና በጥያቄ ለማድመጥ አዲስ ገጽታ የተላበሰውን የSBS ራዲዮ አፕ ይጠቀሙ። የሙዚቃ ራዲዮ ጣቢያዎቻችንን , እና ያድምጡ። እንዲሁም የSBS እንግሊዝኛ ፖድካስት አካትቶ የNITV ይስሙ።
የSBS ራዲዮን አፕ በነጻ ዳውንሎድ ያድርጉ
የSBS ራዲዮ አፕ ያለዎት ከሆነ አዲሱ አፕ ዝግጁ ሆኖ ይጠብቅዎታል። ወደ አፕ ስቶር ያምሩ (የአይፎን ተጠቃሚዎች) ወይም ወደ ጉግል ፕሌይ (የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች) ከዚያም ስክሪን ላይ ያሉ መመሪያዎችን ይከተሉ።
ፕሮግራሞችን በቋንቋዎ እንደምን ማግኘት እንደሚችሉ
በቅድሚያ አፑን እንደ ከፈቱ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ (ዎች) ይምረጡ።
እንዲሁም ቋንቋዎችን My Audio tabን በመጫን መምረጥ ይችላሉ።
ከላይ በቀኝ በኩል የsettings ምልክትን ይጫኑ።
ከዚያም ‘Language Preferences’ን በመጫን የሚናገሩትን ቋንቋ ያክሉ።
Select languages under My Audio by tapping the settings icon. Source: SBS
ማሰስ
ከስክሪኑ በታች ያለውን ማውጫ በመጠቀም አፑን ያስሱ።
የHome tabን በመጫን በመላው SBS ያሉ አዳዲስ ዝግጅቶችን ይቃኙ።
የRadio tabን በመጫን የቀጥታ ራዲዮ ስርጭትን ያድምጡ።
ከላይ ወደ ግራና ቀኝ በማለዋወጥ ምርጫዎ የሆነውን ጣቢያ ይፈልጉ።
የሚሹትን ጣቢያ አንዴ ፈልገው ካገኙ በኋላ ከላይ በስተቀኝ ካለው ማውጫ ላይ "see schedule” ወይም “see full schedule” የሚለውን ይጫኑ።
እንዲሁም playlistን ለማግኘት "see full list” የሚለውን በመጫን እየተጫወተ ያለውን ሙዚቃና የአርቲስቱን ስም መመልከት ይችላሉ።
ሙሉውን የSBS ፖድካስቶች ለመፈለግ podcast የሚለውን ይጫኑ።
ምርጫዎ የሆኑትንና ሲከተልዋቸው የነበሩትን ፕሮግራሞችና ፖድካስቶች My Audio በሚለው ስር ያገኛሉ።
ምርጫዎ የሆኑ ዝግጅቶችን ይከተሉ
ምርጫዎ የሆኑ ፕሮግራሞች አያምልጥዎ! ዝግጅቱን ለመከተል የራዲዮ ወይም የፖድካስት ፕሮግራምን በመምረጥ “follow” የሚለውን ይጫኑ።
ከዚያም My Audio በሚለው ስር ብቅ ይላሉ። ማሳሰቢያ መስጪያዎችን በSettings አማካይነት መቆጣጠር ይችላሉ።
Discover podcasts in over 60 languages Source: SBS