ለማዲንጎ የቀብር ሥነ ሥርዓት የተቋቋመው ኮሚቴ ቃል አቀባይና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ፕሮግራም መግለጡን አዲስ ማለዳ በረቡዕ እትሙ አመልክቷል።
በዚሁም መሠረት ከቀብር ሥነ ሥር ዓቱ በፊት የሽኝት ፕሮግራም ይካሔዳል፤ ዝርዝር መርሃ ግብሩም በቀጣይነት እንደሚነገር ተጠቅሷል።
ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 17 ቀን 2015 ከጠዋቱ 1:30 አክባቢ ለሀኪሙ ስልክ በመደወል ወደ ክሊኒከ እንደሔደና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ የግል ክሊኒክ የሕመም ማስታገሻዎችንና ሌሎች መድኃኒቶችን ወስዶ እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የማዲንጎ ሕይወትም ከቀትር በኋላ ከረፋዱ 3 : 00 ሰዓት አካባቢ ማለፉ ተገልጧል።
የድምፃዊ አስከሬን ሕይወቱ ካለፈበት የግል ክሊኒክ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስዶ ምርመራ እየተካሔደ መሆኑን የገለጠው ፖሊስ በቀረበለት አቤቱታ መሠረት የድምፃዊውን ይውሞት መንስዔ ለማጣራት የአስከሬን ምርመራ ውጤቱን እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል።
አዘዞ ተወልዶ በደብረ ታቦር ከተማ ታደገውና ከ19880ዎቹ አጋማሽ አንስቶ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጉዞ ከተቀላቀሉ ድምፃውያን መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ማዲንጎ አፈውርቅ፤ በ1987 "ስያሜ አጣሁላት" በተሰኘው ቀዳሚ የልበም ሥራው ከሙዚቃ አፍቃሪያን ጋር ተዋውቋል።
በ1990ዎቹ "አይደረግም" እና ከቅርብ ዓመታት በፊት "ስወዳት" የተሰኙ ተወዳጅነት ያስገኙለትን የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጮቹ አበርክቷል።
ድምፃው ማዲንጎ ለሕልፈተ ሕይወት ከመብቃቱ በፊት አራተኛ አልበሙን ለአድማጮች ለማቅረብ በመሥራት ላይ ነበር።