የኢትዮ-ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆነ

ኢትዮ-ቴሌኮም አጠቃላይ ካለዉ 100 ቢሊዮን ብር ድርሻ ዉስጥ 100 ሚሊዮን ያህሉን የባለቤትነት ሽያጭ ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ

Fire1.jpg

Frehiwot Tamiru, CEO of Ethio-Telecom. Credit: Supplied

ግዙፉ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮ-ቴሌኮም 10 በመቶ ( 100 ሚሊዮን ) ድርሻዉን ለሕዝብ በይፋ መሸጥ መጀመሩ ጥቅምት 6 ቀን አስታውቋል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያን የኢትዮቴሌኮም ባለድርሻ ለመሆን ዝቅተኛዉ 33 ድርሻ ዋጋዉ 9,900 ብር ከፍተኛው ደግሞ 3,333 ድርሻ ዋጋዉ 999,900 ብር እንደሆነ ታዉቋል።

"በመጀመሪያው ዙር የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ አጠቃላይ የሼር ድርሻ 100 ቢሊዮን ብር ፤ መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው 100 ሚሊዮን ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል" ሲሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል ።
Fire2.jpg
በዚህም የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንዲሆን መወሰኑን ኢትዮ- ቴሌኮም አስታውቋል።

በተጨማሪም የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌ ብር የሚፈፀም ሲሆን፤ ሽያጩ ከጥቅምት 6 እስከ ታሕሳስ 25 ይቆያል ተብሏል።







Share
Published 17 October 2024 10:52am
By Demeke Kebede
Source: SBS

Share this with family and friends