የመልቲቾይዝ ኢትዮጵያ የሬጉላቶሪና ኮርፖሬት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ መታሰቢያ በላይነህ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው እንዳሉት “መልቲቾይዝ (DSTV) በኢትዮጵያ ስፖርት፣ ባሕልና መዝናኛ ዘርፎች እያከናወነ ያለውን ኢንቨስትመንት አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።
ይህ ዓመታዊ የሚዲያ ሾውኬዝም ዲኤስቲቪ በስራ ዕድል ፈጠራ ፧ በባህል፣ ስፖርትና ሀገራዊ ይዘቶች አቅርቦት፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ ብሎም በቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር እያደረገ ያለውን ጉልህ አስዋጽዖ ለማሳየት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
Metasebia Belayneh. Credit: D.Kebede
አቶ መታሰቢያ አክለውም በቅርቡ በኬንያ ናይሮቢ በተከናወነው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የፊልም ጥበብ ተማሪዎች ምርቃት ስነ ስርዓት ኢትዮጵያዊው መልካሙ ኃይሌ ከመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ አካዳሚ ምሩቃን መካከል አንደኛ በመውጣት ወደ ኒዮርክ ፊልም አካዳሚ የሚያኬደውን ከፍተኛ ሽልማት ማሸነፉ አውስተው፤ መልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ ለአንድ ዓመት ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች በንድፈሀሳብና በተግባር ትምህርት የሚሰጥ የአንድ ዓመት ስኮላርሽፕ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ምሩቃን ወደ ኒውዮርክ፣ ቦሊውድና ደቡብ አፍሪካ ለላቀ ከፍተኛ ትምህርት የሚጓዙበትን ሽልማት ያሸንፋሉ፤ ልጃችን መልካሙ ኢትዮጵያ ወክሎ በከፍተኛ ውጤት በማሸነፉ ለላቀ ትምህርት ወደ ኒውዮርክ እንደሚጓዝ” ተናግረዋል፡፡
የመልቲቾይዝ አፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፍልህሉ ባዱጌላ ከደቡብ አፍሪካ በቪዲዮ ባስተላለፉት የመክፈቻ መልዕክት “ የአፍሪካን ታሪክና ባህል በመተረክና በስፖርትና መዝናኛ ይዘቶች አቅርቦት ረገድ ከእስካሁኑ በበለጠ እንደሚሰሩ ገልፀው፤ በተለይ ለቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ስርጭት ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን” አውስተዋል፡፡
የመክፈቻ ንግግር የክብር እንግዳው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ “ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለኢትዮጵያውያን ትኩረት ያደረጉ የቴሌቪዥን ቻነሎችን ይፋ ያደረገው ዲኤስቲቪ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመንግስት ትውልድና ሀገርን የመገንባት ኃላፊነትን በማገዝ ረገድ ሃላፊነቱ እየተወጣ ያለ ተቋም ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
Mohammed Idris. Credit: D.Kebede
Ambassador Mesfin Cherinet. Credit: D.Kebede
ባልተለመደ መልኩ የቀረበውና በታዳሚዎች ዘንድ አድናቆት የተቸረው የ”አደይ ፋሽን ሾው”ም ቀርቧል። በአቦል ቴሌቪዥን በየዕለቱ የሚተላለፈውን የአደይ ድራማ ገጸ በህሪያት አልባስትን ዲዛይኖች በምታዘጋጀው ዲዛይነር ዳግማዊት ተስፋዬ ዲዛይን የተደረጉና በድራማው ጥቅም ላይ የዋሉ የኢትዮጵያ ባህል አልባሳት በዘመናዊ መልክ ተዘጋጅተው በመድረኩ ቀርበዋል፡፡
Adey Fashion Show. Credit: D.Kebede
ወጣቱ ተወዳጅ ድምጻዊ እሱባለው ይታየው በመሀሪ ብራዘርስ ባንድ ታጅቦ አደይ የተሰኘውን የተከታታይ ድራማው ማጀቢያ ሙዚቃውን በድንቅ ብቃት አቅርቦ ታዳሚውን ያዝናና ሲሆን በአቦል ቴሌቪዥን የሚቀርበው የ”ሚዩዚኮሎጅ” የሙዚቃ ሾው አዘጋጁ ሔኖክ መሐሪም ተወዳጅ ሙዚቃውን በመድረኩ ተጫውቷል፡፡
የአደይ ድራማ ተዋናዮቹ በእምነት ሙሉጌታ (አደይ) እና ሰርካለም ጌታሁን (ሮማን) በየዕለቱ በሚከናወነው የድራማው የፕሮዳክሽን ቀረፃ እንዲሁም የትወና ጥበብ ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን የአላቲኖስ ፊልም ሰሪዎች ማህበር ፕሬዝደንቱ ምኒልክ መርዕድ “አደይ ድራማ በቀረፃና ይዘት የተዋጣለትና በአዳዲስ ቴክኖኮችም የታገዘ ነው” ሲል ሙያዊ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
MS - 2022. Credit: D.Kebede
በመድረኩ ልምዳቸውን ያጋሩት አርቲስቶቹ ዲኤስቲቪ ለኢትዮጵያ ፊልም ዕድገት በፋይናንስና በሚዲያ ስርጭት እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ የሚደነቅና ሌሎችም ሊከተሉት የሚገባ ነው ተናግረዋል፡፡
MS - 2022. Credit: D.Kebede
የሊጎች መጠናከር ለሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፀው ዋና አሰልጣኝ ውበቱ ሱፐርስፖርት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እያበረከተ ያለውን ሁለንተናዊ አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥልም እምነቱን ተናግሯል፡፡
በሾውኬዙ ከሱፐርስፖርት ጋር በመስራት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ተንታኞችና የፕሮዳክሽን ባለሙዎች ልምድም በዶክመንተሪ ፊልም ቀርቧል፡፡
MS - 2022. Credit: D.Kebede
በየዓመቱ የሚከናወነው የመልቲቾይስ ዓመታዊ የሚዲያ ሾውኬዝ በሁሉም የአፍሪካ አገራት የሚከናወን ሲሆን በኢትዮጵያም በየዓመቱ ጥቅምት መጀመሪያ ይከናወናል፡፡ መልቲቾይስ አፍሪካ “ሱፐርስፖርት፣ ዲኤስቲቪ፣ ኤም-ኔት እና ኤርዴቶ” የተሰኙ ታላላቅ ኩባንያዎችን በስሩ ያቀፈ የአፍሪካ ግዙፉ የስፖርትና መዝናኛ ይዘቶች አቅራቢ ሲሆን በ50 የአፍሪካ አገራት እየሰራ ይገኛል፡፡