የፊልም ባለሙያ መልካሙ ኃይሌ ለኒውዮርክ የፊልም አካዳሚ ተመራጭነት በቃ

ኢትዮጵያዊው ወጣት የፊልም ባለሙያ መልካሙ ኃይሌ ከMultichoice Talent Factory ምስራቅ አፍሪካ አካዳሚ የ 2022 ምሩቃን መካከል አንደኛ በመውጣት ወደ ኒውዮርክ ፊልም አካዳሚ የሚያስኬደውን ከፍተኛ ሽልማት አሸነፈ።

Melkamu Haile.jpg

Melkamu Haile (C). Credit: Demeke Kebede

ትናንት ጥቅምት 2 በኬንያ - ናይሮቢ በተከናወነው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የፊልም ጥበብ ተማሪዎች የምርቃት ሥነ ሥርዓት ነው አሸናፊነቱ ይፋ የተደረገው።

መልቲቾይዝ ታለንት ፋክተሪ ለአንድ ዓመት ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የሚሰጥ ስኮላርሺፕ ሲሆን፤ በስልጠናና የተግባር ትምህርት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ምሩቃን ወደ ኒውዮርክ፣ ቦሊውድና ደቡብ አፍሪካ ለላቀ ከፍተኛ ትምህርት የሚጓዙበትን ሽልማት ያሸንፋሉ።
Melkamu Haile (R).jpg
Melkamu Haile (R).
ኢትዮጵያዊው መልካሙ ኃይሌ አንደኛ በመውጣቱ ኒውዮርክ የሚጓዝ ሲሆን የኬንያ እና የታንዛኒያ ምሩቃን ወደ ሕንድ ቦሊውድና ወደ ደቡብ አፍሪካ ይጓዛሉ።

ከምስራቅ አፍሪካ አገራት ከተውጣጡ 19 ምሩቃን መካከል ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣት የፊልም ባለሙያዎች በኬንያ ናይሮቢ የፊልም ጥበብ ሲማሩ ቆይተዋል።

[ ደመቀ ከበደ ፡ ናይሮቢ ኬንያ ]

Share
Published 13 October 2022 9:23am
By Demeke Kebede
Source: SBS

Share this with family and friends