የናይት ቾይዝ የዘንድሮውን የሜልበርን ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል።
በአየርላንዳዊው ፈረሰኛ ሮቢ ዶላን የተጋለበው የናይት ቾይዝ ተቀናቃኙን ሺላ ላክሶንን ቀድሞ የገባው ልብ ሰቃይ በሆነ የአፍንጫ ርቀት ነው።
ዶላን የሜልበርን ዋንጫን ሲያሸንፍ ይህ የመጀመሪያ ዲዜው ነው።
የወለድ መጠን
የአውስትራሊያ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ መጠን ዛሬ ማክሰኞ ኖቬምበር 5 ባካሔደው የቦርድ ስብሰባ 4 ነጥብ 35 ላይ ረግቶ እንዲቆይ ወሰኗል።
ብሔራዊ ባንኩ ምንም እንኳ የዋጋ ግሽበት ዝግ የማለት መልካም አዝማሚያ ቢያሳይም የሚገኝበት ደረጃ ከፍ ያለ ነው ሲል አመላክቷል።
ሆኖም፤ ባንኩ ቀደም ሲል የወለድ መጠንን ለመቀነስ የዋጋ ግሽበት ከ 2 እስከ 3 ፐርሰንት ላይ ደርሶ ማየትን እንደሚሻየገለጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የአውስትራሊያ የዋጋ ግሽበት የሚገኘው ከ3.8 ወደ 2.8 ወርዶ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ዕጩዎች አንዲት ቀን ብቻ ለቀረው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምረጡኝ ዘመቻቸውን አግለው እያካሔዱ ነው።
የሪፕብሊካን ዕጩው ዶናልድ ትራምፕና የዲሞክራት ዕጩዋ ካማላ ሃሪስ ከ270 የምርጫ ኮሌጅ ድምፆች ውስጥ 19ኙ በሚገኝበት ፔንሴልቫኒያ ደጋግመው በመገኘት የምርጫ ቅስቀሳዎቻቸውን አካሂደዋል።
የአውስትራሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና መከላከያ ሚኒስትር ሪችድ ማልስ፤ ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚደንት ሆነው ቢመረጡ የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚኒ ክህሎት ላይ አንዳችም ጥርጣሬ እንደማይገባቸው ገልጠዋል።