የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ጋሻው በ1868 ዓ.ም. ከመቅደላ ጦርነት በኋላ ተዘርፈው ከተወሰዱ በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶች አንዱ መሆኑን አውስቶ፤ ከስኬታማ ስምምነት ላይ መደረስ መቻሉ "ጥልቅ ታሪካዊ ሚናና ባህላዊ ትርጉም አለው" ሲል በይፋ መግለጫው አብስሯል።
አያይዞም " ባለፈው የካቲት ወር ጨረታ ላይ ሊውል የነበረው የመቅደላ ጋሻ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባቀረበው የይገባኛል ጥያቄ መሠረት እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ፣ በልዑል ኤርሚያስ ሣኅለ ሥላሴ መሪነት፣ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት፣ የተቋቋመበትን ዓላማ መመርያ በማድረግ፣ የተዘረፈው ጋሻ ወደ አትዮጵያ በክብር እንዲመለስ ስኬታማ ድርድር ለማድረግ ችሏል" በማለት እንደምን ከስምምነት ላይ እንደተደረሰ ሂደቱን አመላክቷል።
የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቢርት ፕሬዚደንት ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ በበኩላቸው “ይህ ጋሻ ታሪካዊ ቅርስ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ የብዙ ሺ ዘመናት ታሪክ ነፀብራቅ፣ የሕዝባችንን አትንኩኝ ባይነትና ጥቃት የመቋቋምና የመከላከል ብቃቱ ማሳያና ምልክትም ጭምር ነው”
“የኛ የተሳካ ድካምና ልፋት ላለፉት 156 ዓመታት ከኢትዮጵያ ተሰውሮ የነበረው የመቅደላ ጋሻ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ለማስማማት መቻላችን፣ የሀገራችንን ውርስና ቅርስ ለማስጠበቅ፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበርና ለምንወዳት ሀገራችን መስዋዕት የከፈሉ አባቶቻችንን ለማክበርና ታሪካቸውን ለመዘከር ያለንን ቁርጠኝነት ይመስክራል” በማለት የጋሻውን ብሔራዊ ቅርስነት ፋይዳና የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ሀገራዊ አስተዋፅዖ አመላክተዋል።
His Imperial Highness Prince Ermias Sahle-Selassie Haile-Selassie, President of the Crown Council of Ethiopia with the historical Shield of Mekdela. Credit: Crown Council of Ethiopia
“ይህንን ባህላዊ ቅርስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስረከብ ከልዑል ኤርሚያስና ከኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ጋር ለመስራት በመቻሌ ከፍተኛ ክብር ተሰምቶኛል”
“ቤተሰቦቻችን ለብዙ ዘመናት የኢትዮጵያዊያን ዉርስና ቅርስ በክብር እንዲጠበቅ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ብዙ ለፍተዋል። በእጃችን ያስገባነው ጋሻ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልሰን ለማስረከብ ከስምምነት መድረሳችን በቤተሰቦቻችን የተጀመረው ቅርስ የማስመለስ አኩሪ ታሪክ በኛ እንደቀጠለ ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል።
የመቅደላ ጋሻ ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 27, 2024 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ውስጥ ወደ ታሪካዊ ሥፍራው ኢትዮጵያ ከመመለሱ በፊት በተሰኘው ኤግዚቢሽን፣ በToledo Museum of Art ለትዕይንት ይቀርባል።
በወርኅ ሕዳር ወደ ኢትዮጵያ በክብር ተመለሶ፣ በብሔራዊ ሙዚያም ታሪካዊ የሀገቅርስነቱን ጠብቆ ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዕይታ የሚቀርብ ይሆናል።